Tag: oromia

በአማራና በኦሮሚያ መረጋጋት እየመጣ ነው?

ዋዜማ- በአማራና በኦሮሚያ ክልል በመንግስትና በአማፅያን መካከል የቀጠለው ግጭት የበርካታ ዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከማስተጓጎሉም በላይ ቀላል የማይባሉ ዜጎችን ህይወትም እየቀጠፈ ነው። መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች መረጋጋት…

ኦነግ ሸኔ አዲስ ዘመቻ ጀምሯል?

ዋዜማ- ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፣ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ከወትሮው በተለየ መልኩ ተከታታይ ውጊያ እያካሄደ ስለመሆኑ ዋዜማ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች  ካሉት ምንጮቿ…

የደራ ነዋሪዎች  በሁለት ወገን ታጣቂዎች መከራና እንግልት እየደረሰብን ነው አሉ

ዋዜማ- የአማራና የኦሮሚያ ክልል በሚዋሰኑበት የሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ሁለት ፅንፍ የያዙ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑንና በርካቶችም ለመፈናቀል እንደተገደዱ ለዋዜማ ሪፖርተር ተናግረዋል።  በሰሜን ሸዋ ዞን…

“የኦሮሞን ህዝብ ከቀየው አዲስ አበባ መግፋትና ማሳደድ አክትሞለታል” ሽመልስ አብዲሳ

ዋዜማ- የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በግፍና በኢ-ፍትሀዊነት  ከቀየው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) እንዲሰደድ የተደረገውን የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ቀደመ ስፍራው  እንዲመለስ እያደረግን ነው ሲሉ በይፋዊ ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።…

የኦሮምያ ክልል መንግስት የአመራር ለውጥ ሊያደርግ ነው

ዋዜማ- በኦሮምያ ክልል መንግስት ከዘርፍ ቢሮዎች አንስቶ እስከ ዞን ድረስ በሁሉም መዋቅሮች የአመራር ለውጥ ሊደረግ መሆኑን ዋዜማ ከሁነኛ ምንጮቿ ሰምታለች። የክልሉ ምክር ቤት  (ጨፌው) ትናንት መደበኛ ስብሰባውን የጀመረ ሲሆን በዚህ…

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለምን አልተስማሙም?

ዋዜማ- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (አልያም በፌደራሉ መንግሥቱ አጠራር ኦነግ-ሸኔ) እና የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ባደረጓቸው ኹለት ዙር ድርድሮች ወደ ስምምነት ለመድረሰ ተቃርበው ነበር። በኹለተኛው ዙር ድርድር የመጨረሻ ሰዓት ላይ በተፈጠረ አለመግባባት፣ ተስፋ…

ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የህልውና አደጋ አንዣቦበታል

ዋዜማ – ከጥቂት ዓመታት በፊት ሀገሪቱ በቢሊየን የሚቆጠር ብድር አፈላልጋ በሀገሪቱ አስር የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባትና ያሉትን ለማዘመን ስራ ጀምራ ነበር። የብዙዎቹ ግንባታ ተካሂዷል። የኦሞ ኩራዝ አካባቢ አራት ፋብሪካዎች 35 ቢሊየን…

በቦረና ዞን ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ተፈናቅለው በመጠለያ ያሉ  ዜጎች ለከፋ ፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል

ዋዜማ- ለተከታታይ አምስት ዓመታት  ዝናብ በመስተጓጎሉ በተከሰተ አስከፊ ድርቅ  ከ 300 ሺሕ በላይ የቦረና ዞን ነዋሪዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚሁ ተፈናቃዮች ግማሽ ያህሉ ሴቶች ናቸው፡፡ በዞኑ ትልቁ ወደ ሆነው…

በምስራቅ ቦረና ተቃውሞ ትምህርትና የጤና አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት አስቆጥሯል

ዋዜማ- ከአዲስ አበባ 700 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኘው የምስራቅ ቦረና ዞን በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረ አዲስ የዞን አደረጃጀት ነው። በተለይም ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች አንዷ…

በኦሮሚያና አማራ ክልል አዋሳኝ ደራ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 10 ስዎች ሞቱ

ዋዜማ- በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ዋዜማ ተረድታለች። ጥቃቱን የፈጸመው ራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት” ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ…