የደሞዝ ጭማሪው የት ደረሰ? የተከፈላቸው መስሪያ ቤቶች አሉ
ዋዜማ- በጥቅምት ወር ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በመላ ሀገሪቱ ባሉ መንግስታዊ ተቋማት ተግባራዊ ሳይደረግ ሁለተኛው ወር ተገባዷል። ዋዜማ ባደሬችው ማጣራት ደግሞ ቢያንስ የሶስት ተቋማት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ…
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ታገደ
ዋዜማ- ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ እንደተጣለባቸው ዋዜማ ከሚኒስቴሩ በተፃፈ ደብዳቤ ላይ ተመልክታለች፡፡ ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና…
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሶማሊያው መሪ ጋር ከስምምነት ደረሱ
ዋዜማ- ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ፣ በባሕር በር ውዝግብ ሳቢያ በአገሮቻቸው መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቁርሾ ለመፍታት ትናንት ምሽት በፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ኹለቱ አገራት…
የሼኽ መሐመድ ሁሴን አል፡አሙዲ እና የአቶ አብነት ገብረ መስቀል የፍርድ ቤት ክርክር ቀጥሏል
ዋዜማ- ሼኽ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ፣ አቶ አብነት ገብረ መስቀል በፍርድ ቤት የተወሰነባቸውን ከስምንት መቶ ሃምሳ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ መክፈል ካልቻሉ፣ በናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኅ/የተ/የግ/ማኅ/ ውስጥ ያላቸው የ15 በመቶ የአክሲዮን …
ኢትዮጵያ ካሏት 8 የስኳር ፋብሪካዎች በምርት ሥራ ላይ ያለው አንድ ፋብሪካ ብቻ ነው
ዋዜማ- ኢትዮጵያ ካሏት ስምንት ስኳር ፋብሪካዎች በምርት ሥራ ላይ ያለው አንድ የስኳር ፋብሪካ ብቻ መሆኑን ዋዜማ ከየፋብሪካዎቹ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች መረዳት ችላለች። ከስምንቱ ስኳር ፋብሪካዎች መካከል በምርት ሥራ ላይ ያለው ወንጂ…
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብርቱ ጭለማ አለ!
ዋዜማ- የሕዳሴው ግድብ በሚገኝበት ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን የሚገኙ አምስት ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ካገኙ ሰባት ዐመት አልፏቸዋል። በዞኑ በአብዛኛዋ ቦታዎች ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠ ሲሆን፣ በምዥጋ ወረዳ…
“ፋይዳ” ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ያላወጡ ዜጎች በመንግስት ተቋማት አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም
ዋዜማ-በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ስር የሚመራው የብሄራዊ መታወቂያ “ፋይዳ” ያላወጡ ዜጎች በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት እየተጉላሉ መሆኑን አዲስ አበባን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች ለዋዜማ…
ከውጭ የሚገባው ስንዴ የሀገር ውስጥ አርሶ አደሮችን ለኪሳራ እየዳረገ ነው
ዋዜማ- የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ፍጆታ 97 ሚሊየን ኩንታል ይገመታል። ባለፈው ዓመት በበጋ መስኖ እናመርተዋለን ተብሎ የሚጠበቀው የስንዴ ምርት 117 ሚሊየን ኩንታል ነበር። ዋዜማ በዚህ ዓመት በየመንፈቁ ባደረገችው ዳሰሳ ግን አሁንም…
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መምህራን ከደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ አድማ ላይ ናቸው
ዋዜማ- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን፣ የጥቅምት ወር ደምወዝ አልተከፈለንም ያሉ መምህራን፣ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል። በሰሜን…
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ እያቋቋመ ነው
ዋዜማ- መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የካፒታል ገበያ አግልግሎት በሚሰጡ ኩባንያዎች ውስጥ እንዲሳተፉ ባወጣው መመሪያ መሰረት የኢንቨስትመንት ባንክ የማቋቋም ሂደት ላይ መሆኑን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። ንግድ…