Month: November 2022

ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመድን ዋስትና ማግኘት አዳጋች ሆኗል

ዋዜማ- የኢትዮጵያ መንግስት በፖሊሲ ደረጃ ለኤሌክትሪክ መኪና አስመጪ እና አምራቾች ከፍተኛ ማበረታቻዎችን እያደረገ ቢሆንም በሀገሪቱ ያሉ አብዛኞቹ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ግን ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከሶስተኛ ወገን ውጭ ሙሉ የኢንሹራንስ ሽፋን “አንሰጥም”  እያሉ…

በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ አምስት ከተሞችን ያቀፈ”ሸገር ከተማ” የሚል ስያሜ ያለው የከተማ አስተዳደር  ሊቋቋም ነው

ከተሞቹም በአንድ ከንቲባ ይመራሉ ዋዜማ – በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የፊንፊኔ ዙርያ ልዩ ዞን ስር የነበሩ ሰበታ ፣ ቡራዩ ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ፣ ሱሉልታ እና ገላን ከተሞችን በአንድ ያቀፈ “ሸገር…

የመንግስትና የሕወሓት ወታደራዊ አዛዦች የስላም ስምምነቱ ወታደራዊ አፈፃፀም ሰነድን ፈረሙ

ዋዜማ-  መንግስትና ሕወሓት በደቡብ አፍሪቃ በተፈራረሙት የሰላም ስምምነት መሰረት ዛሬ ደግሞ ስምምነቱን መተግበር የሚያስችላቸውን ወታደራዊ አፈፃፀም፣ የመሰረታዊ አገልግሎትና ስብዓዊ ዕርዳታ እንቅስቃሴን የተመለከተ ሰነድ ፈርመዋል።  በኬንያ ናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት የሕወሓት ታጣቂዎች…

 የማዕከላዊ ስታስቲክስ አገልግሎት አራት ከፍተኛ የስራ መሪዎች ከኀላፊነታቸው ተነሱ

ዋዜማ – የማዕከላዊ ስታስቲክስ አገልግሎት ቀድሞ ኤጀንሲ የነበረው ተቋም ዋና ዳይሬክተርና ሶስት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ከኀላፊነታቸው መነሳታቸውን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ስምታለች።  የመስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር ቢራቱ ይገዙ አስቀድሞ ከሀላፊነታቸው…

ዐቢይ አሕመድ በግብፅ ብርቱ የዲፕሎማሲ ስራ ይጠብቃቸዋል

ዋዜማ- ለሁለት ሳምንታት የሚደረገው ዓለማቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (COP27) መክፈቻ ላይ ለመታደም ወደ ግብፅ ያመሩት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዳሴው ግድብ፣ ከሕወሓት ጋር ስለተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ብሎም የብድርና ዕርዳታ…

በመንግስትና በሕወሓት መካከል የተፈረመው ስምምነት አንኳር ነጥቦች 

ዋዜማ- የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓም ደቡብ አፍሪካ ላይ የደረሱበትን የሰላም ስምምነት አስመልክተው ዝርዝር የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። በጋራ መግለጫው ከተካተቱ ዋና ዋና የስምምነቱ ክፍሎች መካከል የሚከተሉት…

የመንግስትና የሕወሓት የጦር አዛዦች ተገናኝተው በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ እንደሚነጋሩ ይጠበቃል።

ዋዜማ – መንግስት እና ህወሓት በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል። ዋዜማ ከመንግሥት ምንጮች እንዳሰባሰበችው ከሆነ ስምምነቱ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ የተባሉ ጉዳዮችን አካቷል።  በደቡብ አፍሪቃ በተፈረመው የሰላም ስምምነት…