Tag: ETHIOPIA

የሳዑዲ በምስራቅ አፍሪቃ መስፋፋት ኢትዮዽያን አስግቷታል፣ ከእስራኤል ጋር ወዳጅነት ለማጠናከር እየተሞከረ ነው

(ዋዜማ ራዲዮ)- በርካታ የምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች የሳዑዲ ዐረቢያ ወዳጅ እየሆኑ ነው። የየመንን ቀውስ ተከትሎ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ኤርትራና ጅቡቲ ከሳዑዲ ጎን ተሰልፈዋል። ይህም የሱኒ እስልምና ዕምብርት የሆነችው ሳዑዲ በምስራቅ አፍሪቃ ከመቼውም ጊዜ…

የኢትዮዽያ ድንበር ጉዳይ ምስጢራዊነትና ስጋት አረብቦበታል

(ዋዜማ ራዲዮ) ኢትዮጵያ ከድንበር ውዝግብ ጋር በተያያዘ አራት ጊዜ ያህል ከጎረቤቶቿ ጋር ወደለየለት ጦርነት ውስጥ ገብታለች፡፡ ከ1983 ዓ.ም ወዲህም የባህር በር አልባ ሆናለች፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር ሲንከባለል የቆየውን የድንበር…

ኤርትራ በየመን ቀውስ ዙሪያ ከሳዑዲና ምዕራባውያን ጎን ተሰለፈች፣ ለኢትዮጵያ መልካም ዜና አይደለም

ኤርትራ በየመን ቀውስ ዙሪያ ከሳዑዲና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጎን መሰለፏን የሚያረጋግጡ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሶስት የጦር መርከቦች አሰብ ወደብ የደረሱ መሆኑን ዋዜማ ያገኘችው የሳተላይት መረጃ ያመለክታል። የመንግስታቱ…

ኤርትራ፣ ኢትዮዽያና ጅቡቲ በየመን ቀውስ ዙሪያ ተፋጠዋል

የኤርትራ የሳዑዲን ፀረ-ሁቲ ወታደራዊ ጥምረት ለመደገፍ ዳር ዳር ማለት ኢትዮዽያንና ጅቡቲን አስደንግጧል። የየመን ቀውስ በአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች ዙሪያ እንደተፈራውና እንደተጠበቀው መፋጠጥ አስከትሏል። ኤርትራ በሳዑዲ ከሚመራው ጥምር ሀይል ጎን ለመሰለፍ መንታ…

በሞላ አስገዶምና ወታደሮቹ ኩብለላ የሱዳን ሚና ምን ነበረ?

ሱዳን የኤርትራ ወዳጅ ሀገር ናት፣ ከኢትዮዽያ ጋር ያላት ግንኙነትም ጥሩ የሚባል ነው። ከኤርትራ ወታደሮች ተዋግቶና አምልጦ ወደ ድንበሯ የገባውን የሞላ አስገዶምን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ቡድን ያለምንም ማንገራገር ወደ ኢትዮዽያ…

የአስመራ ሰዎች በአዲስ አበባ

ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ከአምስት ዓመት በፊት ባወጣው ደንብ በወረራው ወቅት የተባረሩ ኤርትራዊያን እንደገና በኢትዮጵያ ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲያገኙ፣ የቀድሞ ንብረታቸው ከፈለጉም ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው እንዲመለስላቸው ብሎም ከሀገሬው ሰው እኩል ንብረት ማፍራት እንዲችሉ…

“ጦርነቱ”

የአርበኞች ግንቦት 7 አማፅያን በኢትዮዽያ መንግስት ላይ ጥቃት መጀመራቸውን    አስታውቀዋል። መንግስት ጣቱን ወደ ኤርትራ ቀስሯል። ፍጥጫው ክፍለ አህጉራዊ ቀውሱን  ሊያባብሰው ይችላል የሚለው ስጋት ከፍተኛ ነው። ይህን የሶስትዮሽ ፍጥጫ  ተመልክተነዋል።ያድምጡት…

Wazema Alerts- በፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ወቅት የሽብር ጥቃት እቅድ አለ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የምስራቅ አፍሪቃ ጉብኝት ወቅት የሽብር ጥቃት ለማካሄድ የተያዘ ሴራ መኖሩን የዋሽንግተን የደህንነት ምንጮች አመለከቱ። አሜሪካ ዜጎቿ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ ከተቻለም ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት አካባቢ ዝር እንዳይሉ…

“የኢትዮዽያ የብየነ መረብ ደህንነት ተቋም INSA ገልቱ መስሪያቤት ነው “

የኢትዮዽያ የብየነ መረብ ደህንነት ተቋም ወይም በፈረንጁ ቃል INSA ገልቱ መስሪያቤት ነው ሲል የራሱ የስለላ ሸሪክ ወነጀለው። ኢንሳ የኢሳት (ESAT) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነዐምን ዘለቀን ለማጥመድ ብዙ መድከሙን የሚጠቁም መረጃ ይፋ…