Tag: ETHIOPIA

በአማራ ክልል ያለው ዉጥረት ተባብሷል፣ የክልሉ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ተጠይቋል

ዋዜማ- የፌደራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኀይልን አፍርሶ በሌሎች መዋቅሮች ለማደራጀት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞና የፀጥታ ቀውስ አምስተኛ ቀኑን ይዟል። ዋዜማ ባሰባሰበችው መረጃ ትናንት በአማራ ክልል አስራ አንድ…

የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም ስምምነት ትግበራ ክትትል ሐላፊነቱን ለመንግስትና ለሕወሓት ሊተው ነው

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ወሳኝ የሚባል ምዕራፍ ላይ ደርሷል። በቀጣይ ሳምንታት አደራዳሪዎች የስምምነቱን አፈፃፀም ዕውቅና ሰጥተው ቀሪውን ስራ ለመንግስትና ለሕወሓት የሚተውት ይሆናል። መንግስት ከሚያዚያ አጋማሽ በፊት በስምምነቱ የሚጠበቅበትን ለመፈፀም ጥድፊያ…

ስጋ አምራችና ላኪዎች ከዛሬ ጀምሮ ምርት መላክ እናቆማለን አሉ

ዋዜማ- መንግስት በስጋ ላኪዎች የስራ ዘርፍ እየተባባሰ የመጣውን የውጪ  ምንዛሪ ስወራ ማስቆም ስላልቻለ ስጋ ወደ ውጪ ሀገር እንደማይልኩ አስታወቁ።  በውስጡ አስር ዋና ስጋ አምራችና ላኪ ኩባንያዎችን የያዘው ፣የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና…

በብር ሕትመት ተጠምዶ የሰነበተው መንግስት የተጨማሪ በጀት ዕቅድ እስካሁን አለቀረበም

ዋዜማ – ባልተለመደ ሁኔታ ለዚህኛው በጀት አመት እስካሁን ድረስ የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ በጀት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ አላጸደቀም። ለወትሮ በየአመቱ ጥር ወይም የካቲት ወር ላይ የፌዴሬል መንግስት ለአመቱ ከሚይዘው…

ሰሞኑን ከ83ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከሶማሌላንድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል

ዋዜማ- ባለፉት ሳምንታት በሱማሌላንድ ላስ አኖድ ከተማ የተቀሰቀሰውን ግጭት የሸሹ ከ83ሺ በላይ ስደተኞች የኢትዮጵያን ድንበር በማቋረጥ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን እንደሚገኙ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች፣ህፃናት፣ነፍሰ…

የፀጥታና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ባለሀብችን ለመሳብ እንቅፋት እንደሆኑበት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ዋዜማ- የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደርና የውጪ ምንዛሪ ዕጥረት  ችግሮች የውጪ ባለሀብቶችን በበቂ ለመሳብ እንቅፋት እንደሆኑበት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።  የውጭ  ጉዳይ ሚንስቴር የ2015 ዓ.ም የስድስት ወራት አቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ጥር 24…

ኢትዮጵያ ከገዛቻቸው ስድስት የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ መሳሪያዎች አራቱ ያለፉትን 5 ዓመታት ስራ መጀመር አልቻሉም

ዋዜማ- እያንዳንዳቸው አንድ መቶ ሚሊየን ብር የወጣባቸው ስድስት የካንሰር የጨረር ህክምና መሳሪያዎች መካከል አራቱ ያለፉትን አምስት ዓመታት ያለ አገልግሎት መጋዘን ተቆልፎባቸው ይገኛሉ።  የካንሰር ሕሙማን የጨረር ሕክምና ለማግኘት ከአንድ ዓመት በላይ…

 የማዕከላዊ ስታስቲክስ አገልግሎት አራት ከፍተኛ የስራ መሪዎች ከኀላፊነታቸው ተነሱ

ዋዜማ – የማዕከላዊ ስታስቲክስ አገልግሎት ቀድሞ ኤጀንሲ የነበረው ተቋም ዋና ዳይሬክተርና ሶስት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ከኀላፊነታቸው መነሳታቸውን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ስምታለች።  የመስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር ቢራቱ ይገዙ አስቀድሞ ከሀላፊነታቸው…