ዋዜማ ራዲዮ- በኢትዮጵያ የተከሰተውን ህዝባዊ አመፅ ተከትሎ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመነጋገር መድረክ አዘጋጅቷል። ለውይይትና ለድርድር ቅን ልቦና ከሚጎድለው ኢህአዴግ ጋር ለመደራደር መሞከር ከንቱ ድካም ነው የሚሉ ብዙ ናቸው። ከዚህ ቀደም የተደረጉ የድርድር ሙከራዎችን ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ያዋለው ገዥው ፓርቲ ስለምን አሁን ቅን ልቦና ሊኖረው ይችላል ሲሉ ይሞግታሉ። ድርድር የፖለቲካ አለመግባባቶችን ለመፍታት ተመራጩ መንገድ ነው የሚሉት ወገኖች ደግሞ በብልሀት የሚደረግ ድርድር የጤናማ ፖለቲካ አካሄድ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። ዶ/ር ደረሰ ጌታቸውና መስፍን ነጋሽ የሰሞኑን የድርድር ድግስ አፍታተው ይመለከቱታል። አርጋው አሽኔ አወያይቷቸዋል። አድምጡና የናንተን ሀሳብ ደግሞ አጋሩን።