18641326_1354674071312375_369839678_oዋዜማ ራዲዮ- በሀዋሳ የሚገነባው ግዙፍ የኢንደስትሪ ፓርክ በሀዋሳ ሀይቅ ላይ ከፍ ያለ የብክለት አደጋ ሊያደስ የሚችል ግንባታ እያደረገ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች አመለከቱ።
ይህ ግዙፍ የኣኢንደስትሪ ፓርክ በርካታ ፋብሪካዎችንና የማምረቻ ተቋማትን የያዘ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የማስተላለፍ አቅም ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ እየቀደደ መሆኑን የዋዜማ ሪፖርተር በቦታው ተገኝታ ተመልክታለች።
የፍሳሽ ማስወገጃው ከሀዋሳ ሀይቅ ጋር እንዲገናኝ መደረጉ ስጋት የፈጠረባቸው ነዋሪዎች ጉዳዩን በሀገር ቤት ላሉ የመገናኛ ብዙሀን ቢያቀርቡም ስሚ እንዳላገኙ ገልፀውልናል።
የፍሳሽ ማስወገጃው የተጣራ ፈሳሽ ቆሻሻን ብቻ ለማስወገድ የሚውል መሆኑን የአዋሳ ከተማ አስተዳደር ለነዋሪው ሲገልፅ ቢቆይም አሁን ከግንባታ ባለሙያዎች በተገኘ መረጃ የኣኢንደስትሪ ፓርኩ ምንም አይነት የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ማከሚያ እንደሌለው ለመረዳት ተችሏል። ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው የደቡብ ክልል የኣአካባቢ ጥበቃና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ባለሙያዎች የኣኢንደስትሪ ፓርኩ የፈጠረውን ስጋት እንደሚጋሩ ገልፀው ጉዳዩ የፌደራል መንግስት በመሆኑ አስተያየት ለመስጠት እንቸገራለን ብለዋል።
ለኣኢኮኖሚ አገልግሎትም ሆነ ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነው የሀዋሳ ሀይቅ ባለፉት አስራ አምስት አመታት በኣአቅራቢያው በተደረጉ የተለያዩ ግንባታዎች ለብክለትና ለውሀ መጠን መቀነስ ተጋልጦ ቆይቷል።
ለሀዋሳ ከተማ ልዩ መሽብ የሆነው ይህ ሀይቅ በኣአፈጣጠሩ እምብዛም ጥልቀት የሌለው በመሆኑ ሳቢያ በቀላሉ ለ አደጋ የተጋለጠ ነው። 18597025_1354670517979397_1620820697_o