Azeb Asnake former CEO of EEPCO

ዋዜማ ራዲዮ- ከህዳሴ ግድብ ደን ምንጣሮ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር አዜብ አስናቀ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ50 ተከሳሾች ላይ ስልጣንን ያለአግባብ የመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት መስርቷል፡፡

ነገር ግን አቃቤ ህግ ክሱን ካቀረበባቸው ተከሳሾች ውስጥ ኢ/ር አዜብን ጨምሮ 43ቱ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ናቸው፡፡

አቃቤ ህግ 1ኛ ተከሳሽ አድርጎ በክሱ ያካተታቸው የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮ/ል ሙሉ ወልደገብርኤል፣ ኮ/ል ያሬድ ሀይሉ እና ኮ/ል ሰሎሞን በርሄ ደግሞ ከዚህ ቀደም ሌላ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ናቸው፡፡

ዛሬ በችሎት የቀረቡት 10፣14፣25 እና 42ኛ ተከሳሾች ሲሆኑ ችሎቱ ክሳቸውን በዝርዝር አንብቦላቸዋል፡፡

በ1996ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1) ሀ ፣ለ 33 እና 407(1) ሀ፣ለ እና (2) ስር የተደነገጉት ህጎች ተጥሰዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ክስ የመሰረተው አቃቤ ህግ ፡-

የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የግድቡ ውሀ የሚያርፍበትን 123 189 ሄክታር ስፋት ያለው ደን የመመንጠር እና የማፅዳት ስራ በ5ቢሊዮን158 ሚሊዮን 611ሺህ 519 ብር ለመስራት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር ህዳር 16 ቀን 2007 ዓም ውል ማሰሩ ተገልጽዋል፡፡

በ1ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች አማካኝነት የተፈረነው ውሉ ላይም ስራው በሁለት አመት ውስጥ ማለትም ህዳር 16 ቀን 2009 ዓም መጠናቀቅ እንዳለበት ሰፍሯል ይላል፡፡

የውሉን 50 በመቶ ክፍያ ማለትም 2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሀይል ስለመቀበሉም በክሱ ተጠቅሷል፡፡

ነገር ግን ከአራት አመታት በኋላ ማለትም የፌደራል ዋና ኦዲተር ኦዲት ሪፖርቱን አጠናቆ እስካቀረበበት 2011 ድረስ 31 በመቶ የሚሆነው ስራ ብቻ መሰራቱን አቃቤ ህግ በክሱ ገልፅዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ ከተቀበለው 50 በመቶ ክፍያ ላይ 23 በመቶ ብቻ የሚሆነው ለሰራተኞች የተከፈለ ሲሆን ቀሪ 1.9 ቢሊዮን ብር ምን ላይ እንደዋለ አይታወቅም ሲል ገልፅዋል

ይህም በኮርፖሬሽኑ ላይ 1ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ያደረሱት ኪሳራ ነው ሲል ገልፅዋል፡፡

ሌሎች ተከሳሾች ደግሞ የደን መመንጠር ስራውን የተረከቡ ድርጅቶች ያልተመነጠረውን የደን ሄክታር እንደተመነጠረ በማስመሰል ከአግባብ በላይ ክፍያ እንዲፈፀም ስለማድረጋቸው የአቃቤ ህግ ክስ ያስረዳል፡፡

በዚህም በብልጫ የተከፈለ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ያለ እናዳለ አቃቤ ህግ በክሱ ገልፅዋል፡፡

አቃቤ ህግ ኢ/ር አዜብን እና ሌሎች 2 ተከሳሾችን በሚመለከት ባቀረበው 2ኛ ክስ ደግሞ በሁለት አመት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ውሉ ቢያዝም የውሉ ጊዜ በተጠናቀቀበት ወቅት 30 በመቶ ብቻ ተሰርቶ እያለ ውሉ ያለ አግባብ እንዲሻሻል ማድረጋቸውን ገልፅዋል፡፡

አክሎም የመጀመርያው ክፍያ ስራው 50 በመቶ ሲጠናቀቅ ከአጠቃላይ ክፍያው 30 በመቶ ይከፈላል የሚለውን ያለአግባብ በማሻሻል ስራው 30 በመቶ ሲጠናቀቅ የ30 በመቶ ክፍያ እንዲከፈል በማለት ማሻሻላቸውን እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ያለ አግባብ እንዲከፈል ማድረጋቸውንም ክሱ ያስነብባል፡፡

በተጨማሪም የጨረታ ሰነድ ከሚያዘው ውጭ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ መከፈል እንደሌለበት ቢገለፅም ኢንጅነር አዜብ እና አቶ አብይ ይሁን ከሜቴክ ጋር የስራ ውል ሳይፈፀም በፊት 500 ሚሊዮን ብር ያላአግባብ እንዲከፈል ስለማድረጋቸውን የአቃቤ ህግ ክስ ያስነብባል፡፡

በችሎት የቀረቡት 4 ተከሳሾች ክሱ ከተነበላቸው በኋላ ሁለቱ ጠበቃ የማቆም አቅም የሌላቸው መሆኑን ለችሎቱ በመሀላ በማስረዳት የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው ተወስኖላቸዋል፡፡

እንዲሁም የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም አቃቤ ህግ የተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ በመሆኑ የዋስትና መብትን ያስነፍጋል በማለት ጥያቄውን ተቃውሟል፡፡

ችሎቱ በዋስትና ክርክሩ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እና በማረምያ ቤት ላሉ ተከሳሾች ክሳቸውን ለማንበብ ለእሮብ ቀጠሮ ሰጥቷል፡

ከህዳሴ ግድብ ደን ምንጣሮ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር አዜብ አስናቀ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

የተከሳሾቹ ዝርዝር የሚከተለው ነው

1. ኮ/ል ሙሉ ገብርኤል ገ/እግዚአብሄር.

-ስራ፡- የበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ም/ዋና ዳይሬክተር እና የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ኃላፊ የነበሩ

2. ኢ/ር አዜብ አስናቀ 

-ስራ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩ

3. አቶ ብረዳ ማሩ

-ስራ ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፖርት ፎሊዮ ማናጅመንት ስራ አስፈፃሚ የነበሩ

4. አቶ አብይ ይሁን

-ስራ ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ ኃላፊ የነበሩ

5. ኮ/ሌ ያሬድ ኃይሉ ገብረዮሃንስ

-ስራ ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት  ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኃላፊ የነበሩ

6.ሌ/ኮሎኔል በርሄ አበበ 

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት የፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊ የነበሩ

7.ሎ/ኮሎኔል ለተብርሃን ደሞዝ ተ/ሚካኤል

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት የፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊ የነበሩ

8. ሻ/ል አሊ አደም መሃመድ

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን  የህዳሴ ግድብ የደን ምንጣሮ ፕሮጀክት  ኃላፊ የነበረ(ልኬት አፀዳቂ)

9. ሻ/ል ጌታቸው ገ.ስላሴ ተፈራ

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን  የህዳሴ ግድብ የደን ምንጣሮ የሳይት ኃላፊ የነበረ(ልኬት አረጋጋጭ)

10. ሻ/ቃ ፍቃዱ ጋሻው ጌቱ

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን  የሰው ኃይል ልማት  ኃላፊ የነበሩ

11. ም/መ/አ/ ሀብታሙ ድፍሩ

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን  የህዳሴ ግድብ የደን ምንጣሮ ፕሮጀክት (ልኬት ተረካቢ የነበረ)

12. ባይሳ ሂርጳ

-ስራ፡- በበረታ ብረትና  ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን  የህዳሴ ግድብ የደን ምንጣሮ ፕሮጀክት (ልኬት ተረካቢ የነበረ)

13. ተወልደ ካሳሁን

-ስራ ፡- ፍቼ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህነር ስራ አስኪያጅ

14. ጉዑሽ ካሳ ደሞዝ

-ስራ ፡- ጂዲጂ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

15. ዳንኤል ፀጋዬ ገ/እየሱስ

-ስራ ፡- ጂዲጂ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር አስረካቢ የነበረ

16. ልዑል ሀብቱ

ስራ፡- የውህደት ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

17 . የይብራህ ገብረ ገብረዋህድ 

-ስራ ፡- የይብራህ ገብረ ህንጸ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ስራ አስኪያጅ

18. ሀፍቶም ገ/እግዚአብሄር

-ስራ ፡- የቤተሳሌም ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

19. ኮ/ሌ መንግስቱ ከበደ

-ስራ፡- ምዕባለ ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

20. ሻሹ ዳኘው ገ/ስላሴ

-ስራ ፡- ቀዳዊት ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

21. ባይሳሳው ደስታ

-ስራ፡ ቀብሪደሃር ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

22. እሱ ባለው ተገኘ

-ስራ ፡- እሱባለው ተካልኝ ስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

23. ሃ/አለቃ አበራ ሰቦቃ

-ስራ ፡- እኛን ነው ማየት ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

24 . ሻለቃ ተስፋዬ ታንቱ 

-ስራ፡- ጁፒተር ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

25. ግርማ ቤክሲሳ

-ስራ ፡- የግርማ ቤክሲሳ ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

26. አባይ ታርቆ

-ስራ፡- የዘላቂ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

27. ፍፁም በየነ

-ስራ፡- የፍሬህይወት በየነ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ስራ አስኪያጅ

28. ኑር ሁሴን መ/ሳለህ 

-ስራ ፡- ሬድኮን ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

29. ዳዊት ሰለሞን

-ስራ፡- ቀብሪድሃር ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

30. ገ/መድህን ሀይለ

-ስራ፡- ገ/መድህን አረጋዊ ብርሃኔ ኮንስትራክሽን ህ/ሸ/ማ ስራ አስኪየጅ

31. ጎይቶም መኮንን

-ስራ፡- ጎይቶም መኮንን ህንጻ ስራ ተቋራጭ ስራ አስኪያጅ

32.መ/አለቃ አለሙ ረዲ

-ስራ፡- ዋንዛ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ

33.ሌ/ኮ/ል ፋሲል አፅፈ ጊዮርጊስ – ሰንጉያ ብረታ ብረት እና ኮንስታራክሽን 

34. መሀሪ ገ/እግዚአብሄር -መሀሪ ገ/እግዚአብሄር  ጠቅላላ ንግድ ስራ ተቋራጭ 

35. አማን ኢብራሂም- ገረብ ኮንስትራክሽን

36. ብርሀነ ገ/ስላሴ – እንከባበር ኮንስትራክሽን

37. ሌ/ኮ/ል ሸጋው ተ/ማርያም መፈጋገፍ ኮንስትራክሽን

38. ፍፁም ተሸመ – ፍፁም ተሸመ ህንፃ ስራ ተቋጭ 

39. ሹመዲን ገ/ጊዮርጊስ – ሻንሌ ስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

40. ስዬ ሀይሉ – ሌክሰስስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

41. ኮ/ል ተጫነ አባይ ዩኑ አድ ጠቅላላ ስራ ተቋጭ ስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

42. ጋሻውጠና አሰፋ – ማርች ጠቅላላ ስራ ተቋጭ 

43. ዘርዓይ ገብሩ- ቲ.ጂዜድ ኮንስትራክሽን 

44. ገብረገርግስ ተስፋዬ – አቅመራ ኮንስትራክሽ

45- ወልደሩፋኤል ሀይለ- ሙጉላት ጠቅላላ ንግድ

46. ዘርዓይ ወልደማርያም- ስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

47.ሌ/ኮ/ል መሀመድ ሺሞን -ስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

48. ሙሉ ኃ/ሚካኤል – እኛው ለእኛው ኢንተርፕራይዝ

49. ዳንኤል ደረጄ- ዩክሪፕቶናይት ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

50. ፊደል አለምሰገድ- ኤፍ.ኤም.ኤትሬዲንግስራ ተቋራጭ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር

[ዋዜማ ራዲዮ]