ዋዜማ ራዲዮ- አምባገነን ስርዓት ከሚታወቅባቸው መለያዎቹ አንዱ በዜጎች ላይ የሚፈፅመው ግፍና አፈና ነው። አሁን ዘመኑ መረጃ በቀላሉ የሚንሸራሸርበት ሆኖ ስለሚፈፀሙ በደልና ግፎች ከበፊቱ በፈጠነ መንገድ እንሰማለን፣ ሰዎች ምስክርነት ይሰጣሉ፣ የመብት ተሟጋቾች ይወተውታሉ። አሁንም ቢሆን ግን ሰሚ ያላገኙና ተደብቀው ያለ የስብዓዊ መብት ጥሰቶች የትየለሌ ናቸው።  በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ወድቆ በሌላ ሲተካ ተበዳዮች ቁስላቸውን ይዘው አደባባይ ይወጣሉ፣ አንዳንዶች ራሳቸውን ደብቀው ተሸማቀው ይኖራሉ። ገራፊዎቻችን ገዳዮቻችን አሳዳጆቻችን ይህን ሁሉ ሲያደርጉ ይህ እንዲፈፀም የሚፈቅድ መሪ የፖለቲካ ፓርቲና ስርዓት ይሁንታ አግኝተው ነው።  ከእያንዳዱ ገራፊ ጀርባ ስርዓቱና መሪዎቹ  አሉ። ከሰሞኑ የተፈፀመበትን በደል ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የተናገረው የአንድነት ፓርቲ አመራር የነበረው ሀብታሙ አያሌው ዛሬ በሀገሪቱ ስላለው ስርዓት የሚናገረው አንድ ነገር አለ። በርግጥ በርካቶችን በአደባባይ በጥይት በመቅጠፍ ስሙ የሚነሳው የኢህአዴግ መንግስት ዕዳው ከዚህም የከፋ ስለመሆኑ የሚናገሩ አሉ።
የጉዳዩን ፋይዳ  እንዲሁም በዋዜማ ራዲዮ ለሰብዓዊ መብት ጉዳዮች የምንሰጠውን ልዩ ዋጋ መነሻ አድርገን፣ ከበር ጀርባ በዜጎች ላይ በሚፈፀሙ ግፍና በደሎች ዙሪያ ይህን ልዩ መሰናዶ ይዘን ቀርበናል።  አርጋው አሽኔ ከቴክሳስ- ሀኒ ሰለሞን ከዋሸንግተን ዲሲ በጋራ እናስተናግዳችኋለን። ሙሉ የድምፅ ዘገባውን ከታች ያገኙታል 

በዕለቱ የዋዜማ መፅሄት
-ሀብታሙ አያሌው ምን እያለን ነው?
-አሳሪና ገራፊዎቻችን ማናቸው?
-መሪውን የሰቀለ ተበዳይ ምስክርነት..
-የግብፅና ኤምሬትስ የአፍሪካ ቀንድ ጉድ-ጉድ ቀጥሏል!
ዋዜማን አድምጡ አጋሩ

https://www.youtube.com/watch?v=84fOJxZ_DWU