The-Piazza-with-the-city-hall-under-construction-in-the-background

የከተሞች እና የመከተም (urbanization) ነገር በአገራችን ማኅበረሰባዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸው ቦታ ዘመን በገፋ መጠን በእጅጉ እየጨመረ መምጣቱ ቢታወቅም በምርምርም ሆነ በሕዝብ አደባባይ ብዙም አልተባለለትም። ነገሩን ከከተሞች ታሪክ፣ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ፣ ባህላዊ ገጽታ እንዲሁም ፖለቲካዊ ስፍራ አንጻር መመልከት ይቻላል:: በዚህ ዝግጅታችን ስለከተሞች ምንነት፣የኢትዮጵያ ከተሞች በየዘመኑ ከነበሩ መንግሥታት እና ፖለቲካዊ ድባብ ጋራ የነበራቸውን ግንኙነት እናወሳለን። የከተሞች መፈጠርን ግድ የሚለው ነገር ምንድን ነው? ከተማና ገጠር ሲባል በተለምዶ የሚሳለው ምስል እንደምን ያለ ነው፣ ትክክልስ ነው? ከተሞቻችን እና መንግሥቶቻችንስ እንደምን ባጁ? እያለ ውይይቱ ይቀጥላል። የውይይቱ ተካፋዮች ሽመልስ ቦንሳ (ዶ/ር) እና ደረሰ ጌታቸው (ዶ/ር) በየትምህርት ዘርፎቻቸው ስለከተሞች አጥንተዋል፣ ያስተምራሉም። ውይይቱን ትወዱታላችሁ፣ ቢያንስ አንድ ሐሳብ ስለሚያጭርባችሁ።