Category: Current Affairs

ሕወሓት ያቋረጠውን ስብሰባ ይቀጥላል

ዋዜማ ራዲዮ-ከመስከረም 23 ጀምሮ መቀሌ ከትሞ የነበረው የሕወሓት ማዕከላዊ ምክር ቤት ጉባኤ በደኢህዴን ምስረታ በዓል ስብሰባና በማዕከላዊ መንግሥቱ ዙርያ ባጋጠሙ ሌሎች አጣዳፊ ጉዳዮች ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በዚህ ሳምንት ይቀጥላል…

የኦርቶዶክስ ቤተ-ክህነት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ እየተማከሩ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- ብዙ ውጣ ውረዶችና ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የሚፈታተናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክህነት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ለቅርብ ስዎቻቸው በመጪው ሳምንት “ስልጣኔን እለቃለሁ” ማለታቸውን የዋዜማ ምንጮች ነግረውናል። ባለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ…

የሕወሓት የስልጣን ሽኩቻ ተካሯል

ዋዜማ ራዲዮ- የድርጅቱ ብሔርተኛ ካድሬዎች ካልሆኑ በስተቀር እምብዛምም የሕዝብ አለኝታና ድጋፍ የላቸውም የሚባሉት አቶ አባይ ወልዱ የሕወሓትን የሊቀመንበርነት ቦታ ይዞ የመቀጠል እድላቸው ጠባብ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ዶክተር ደብረጺዮን ቦታውም ለመያዝ…

‹ኢህአዴግ ለሁለት የመሰንጠቁ ነገር አይቀርለትም› አቶ በረከት ስምዖን

ዋዜማ ራዲዮ- አቶ በረከት ስምዖን የስልጣን መልቀቂያ ከማቅረባቸው ባሻገር ስለ ኢህአዴግ “መሰንጠቅና”  ስለ “ርዕዮት አለም መስመር አለመታመን” በአደባባይ እየተናገሩ ነው። አቶ በረከት የፓርቲያቸውን ከፍተኛ ካድሬዎች ማጥመቂያ በሆነው ስልጠና ላይ እየሰጡ…

በሻሸመኔው የተቃውሞ ሰልፍ መንገደኞች በግዳጅ እንዲሳተፉ ተደርጓል

ዋዜማ ራዲዮ- በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እየተካሄደ በነበረ በአንዱ ተቃውሞ ሰልፍ ተሳትፎ ያልነበራቸው መንገደኞች በሰልፈኞች ተማርከው በግዳጅ አመጹን እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን ሰምተናል፡፡ በግዳጅ ብንገባም ለመቃወም እድል ስላገኘን አልተከፋንም ይላሉ። ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ…

በሶማሌ ክልል አዲስ ብሄርን ያማከለ የመፈናቀል አደጋ አንጃቧል

ከኦሮሞ ጋር ወግናችኋል የተባሉ የአማራና የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጆች ንብረታቸው እየተቀማ ነው ዋዜማ ራዲዮ- በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች ውስጥ የተነሳው ግጭት ከመብረድ ይልቅ በተለይ በጅግጅጋ (ጅጅጋ) ከተማ መልኩን እየቀየረ መሆኑን ዋዜማ…

የዶላር ጭማሪ አዲስ አበባን እያመሳት ነው

ነጋዴዎች እቃቸውን እያሸሹ ነው፡፡ መርካቶ በዋጋ ተመን መዋዠቅ ግራ ተጋብታለች፡፡ ዋዜማ ራዲዮ-ከትናንት በስቲያ የተደረገውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ ተከትሎ በማግስቱ የጀመረ የዕቃ አቅርቦት ችግርና የዋጋ መዋዠቅ በመዲናዋ በተለይም በመርካቶ በስፋት…

የኢትዮዽያ ቀውስና የጎረቤት ሀገሮች ስጋት

ዋዜማ ራዲዮ- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተባባሰው ዘውግን ያማከለ ግጭት ሀገሪቷን ወደማትወጣው ቀውስ ከመክተት ባሻገር ከጎረቤት ሀገሮች ጋር ሊያናቁረን የሚችል አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ለዚህም አንዳንድ ምልክቶች አሉ። የኢትዮዽያን ቀውስ ጎረቤት ሀገሮች…

አባዱላ በአዲስ ክልላዊ ሃላፊነት መቀጠላቸው እየተነገረ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- ለኦህዴድ ካድሬዎች እንኳ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው የአቶ አባዱላ የሥልጣን መልቀቅ ጥያቄ  እያነጋገረ ነው፡፡ ለፓርቲው ቅርብ ነን የሚሉ ሰዎች የአባዱላን ‹‹ድንገተኛ›› እርምጃ በጥልቅ ታስቦበት የተደረገና አዲሱ የኦህዴድ አመራር…