Assab 2(ዋዜማ ራዲዮ) የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሶስት የባህር ሀይል የጦር መርከቦች በኤርትራ የአሰብ ወደብ ላይ መስፈራቸው ተሰማ።

ዋዜማ ከሁነኛ ምንጮች እንዳገኘችውና የሳተላይት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የጦር መርከቦቹ ያለፉትን ቀናት በአሰብ ወደብ ዳርቻ ሰፍረው የተለያዩ ወታደራዊ አግልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ሀይል አባል በመሆን በየመን ሁቲ አማፅያን ላይ ውጊያ ከከፈቱት ሀገሮች አንዷ ናት። ኤርትራ ከጥምር ሀይሉ ጋር ለመሰለፍ ስታመነታ ብትቆይም በቅርብ ሳምንታት ለመተባበር ፈቃደኛ መሆኗን ፍንጮች ስታሳይ ቆይታለች። ኤርትራ የባህርና የአየር ክልሏን በመፍቀዷ ከሳዑዲና ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ታገኛለች።ሁኔታው ያሳሰባቸው  የኢትዮዽያ የጅቡቲና የሶማሊያ መሪዎች ባለፈው ሳምንት ወዳ ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል። ተጨማሪ ዝርዝር ዘገባ ይዘን እንቀርባለን