Month: January 2022

የሲዳማ ክልል በዘንድሮ ዓመትም ዞን ማዋቀር እንደማይችል አስታወቀ

ዋዜማ ራዲዮ- ከሁለት አመት በፊት 10ኛ የፌደራል ክልል ሆኖ በሕዝበ ውሳኔ የተቋቋመው የሲዳማ ብሄራዊ ክልል በያዝነው 2014  ዓመት የዞን የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋት እንደማይችል አስታወቀ። ዞን ማዋቀር ከወጪ ጋር የሚያያዝና የራሱን…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሶስት አመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ዳይሬክተሮች ምደባ ሊያደርግ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የምክትል ፕሬዝዳንቶችና ዳይሬክተሮች ምደባ ሊያደርግ እየተዘጋጀ መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ ከባንኩ ምንጮች ሰምታለች። የአመራሮቹ ምደባ የሚካሄደው ባንኩ ባካሄደው አዲስ…

የኤፈርት ኩባንያዎችን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድረው ቦርድ ተበተነ

ዋዜማ ራዲዮ- የህወሓት ንብረት የሆኑንት የኤፈርት የንግድ ኩባንያዎች የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የባንክ ሂሳባቸው ታግዶ መንግስት በሰየመው ቦርድ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ግን ስባት አባላት ያለው ቦርድ ስራውን በፈቃዱ ለቆ ተበትኗል።…

በአዲስ አበባ 29 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማጠናቀቅ ብድር ተጠየቀ

ዋዜማ ራዲዮ- በአዲስ አበባ የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የፋይናንስ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ፣ ለቤቶቹ ማጠናቀቂያ ብድር እንዲፈቀድ ለብሔራዊ ባንክ ጥያቄ ቀረበ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ…

ኬንያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ግዥ ልትጀምር ነው

[ዋዜማ ሬዲዮ] የኢትዮጵያና ኬንያ ኃይል ማስተላለፊያ ግንባታ መገባደድን ተከትሎ ኬንያ በቀጣዮቹ ወራት የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ኀይል ግዥ እንደምትጀምር በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለዋዜማ ነግረዋል። ከዓመታት በፊት በኬንያ እና በኢትዮጵያ…

የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ያሳዩ ዓለማቀፍ ተጫራቾች በኩባንያው የወሳኝነት ሚና እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ

ዋዜማ ራዲዮ- አርባ በመቶ የባለቤትነት ድርሻውን ለውጪ ኩባንያዎች ለመሸጥ በሂደት ላይ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ተጫራቾቹ እያሳዩት ባለው የኩባንያውን የአመራር ሰጪነት የመቆጣጠር ፍላጎት ጨረታውን ለማራዘም ሳይገደድ እንደማይቀር ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ…

የአብርሆት ቤተ -መጻህፍትን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ተረክቦ ያስተዳድራል

[ዋዜማ ሬዲዮ]  በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተገንብቶ በቅርቡ  ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የአብርሆት ቤተ-መጽሃፍትን የማስተዳደር ሐላፊነት በጊዜያዊነት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊሰጠው መሆኑንና በሚቀጥሉት ቀናት ርክክብ ሊፈፀም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዋዜማ ከተለያዩ…

የአዲስ አበባ አስተዳደር በጋራ መኖሪያና በንግድ ቤቶች ላይ ጥሎት የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ህትመት እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ

ዋዜማ ራዲዮ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎት ላይ ጥሎት ከነበረው እገዳ መካከል፣ በኮንዶሚኒየም እና ንግድ ቤቶች ላይ የጣለውን የይዞታ ካርታ ህትመት እገዳን በማንሳት አገልግሎት እንዲጀመር አዘዘ።…

የኢትዮጵያ መንግስት የድሕረ ጦርነት የፀጥታና ደህንነት ስጋቶች ላይ እየመከረ ነው

[ዋዜማ ራዲዮ]- የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ሲካሄድ የነበረው ጦርነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል መጠናቀቁን ካወጀ በኋላ በድሕረ ጦርነቱ በሚኖሩ የፀጥታ ስጋቶች ላይ ምክክር ማድረግ መጀመሩን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ማረጋገጥ ችላለች።…