difretበአንዲት ኢትዮጵያዊት ታዳጊ ወጣት ታሪክ ላይ የተመሰረተውድፍረትየተሰኘው ፊልም አርብ ጥቅምት 12 ቀን በአሜሪካ ለሕዝብ መታየት ጀመረ ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው።

14 ዓመት ዕድሜዋ ተጠልፋ  ዕድሜ ጋብቻ የተዳረገችው ታዳጊ ወጣት እንዴት ጠላፊዋን ሳትወድ በግድ እንደገደለችውና ከዚህም የተነሳ ያጋጠማትን ምስቅልቅል ሕይወት የሚያሳይ የታሪክ ይዘት አለው። ፊልሙ በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ሲታይ ይቆያል።

(መዝገቡ ሀይሉ ዝርዝር ዘገባውን በድምፅ አዘጋጅቶታል)

በፊልሙ ዝግጅትም ላይ ከታዋቂዎቹ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊሊያን ደሞዝ እና ጁሊ ምሕረቱ በተጨማሪ አንጀሊና ጁሊን እና ሌሎችንም የምዕራቡን ዓለም ታዋቂ ሰዎች አካቷል። በዚህም ምክንያት አዘጋጆቹ እንዳሰቡት የምዕራቡን ዓለም መገናኛ ብዙኀንና የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ትኩረት ለማግኘት ችሏል።

ፊልሙን ከማስተዋወቅ ጎን ለጎን ያለዕድሜ ጋብቻንና ጠለፋን የመሰሉ ጎጂ ባሕሎች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ አቤቱታም ሲፈረም ቆይቷል። 140 ሺህ ሰዎች በላይ የፈረሙት ይህ አቤቱታ ፕሬዚዳንት ኦባማ ይህን በመሰሉ ሴቶች ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ጎጂ ባሕሎችን የሚመለከት ትእዛዝ እንዲሰጡ የሚጠይቅ ነው።

Julie Meheretu
Julie Meheretu

አንጀሊና ጁሊና ጁሊ ምህረቱ የፊልሙ ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰሮች ቢኾኑም፤ የጁሊ ምሕረቱ አስተዋጽዖ በፊልሙላይ የጎላ ይመስላል። ምክንያቱም 750 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የፈጀውን የፊልሙን ወጪ ለመሸፈን ከዚህ በፊት ሰርታቸው ከነበሩት ስዕሎቿ መካከል አንዱን እንደሸጠች የአሜሪካ መገናኛ ብዙኀን እየተናገሩላት ነው። ያም ኾኖ ከዚህ የፊልም ወጪ ውስጥ ምን ያህሉን እንደሸፈነች አልተገለጸም።

ጁሊ ምሕረቱ ከኢትዮጵያዊ አባት እና አሜሪካዊ እናት የተወለደችና እስከ ሰባት ዓመት ዕድሜዋም ድረስ በኢትዮጵያ ያደገች ስመ ጥር ሰዓሊ ናት። የስዕል ሥራዎቿም የታወቁት በመጠናቸው ትልቅነትና አረብ ስፕሪንግን እና ካቡልን በመሰሉ ቀውስ ባለባቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት አድርጋ በምትሰራቸው ስራዎቿ ነው።

የጁሊ ምሕረቱ ስዕሎች እስካለፈው የፈረንጆች ዓመት ድረስ እስከ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ሲሸጡ ቆይተዋል። ባለፈው ዓመት ግን “Retopistics: A Reneagade” የተባለው ስዕሏ ለጨረታ ቀርቦ ከተጠበቀው በላይ በመገመቱ ለጁሊ ተጨማሪ ዝናን አትርፎላታል። ይህ ስዕል የተሸጠው 4.6 ሚሊዮን ዶላር ሲኾን ጁሊም 10 በውድ ከሚሸጥላቸው በሕይወት ያሉ ሴት ሰዓልያን አንዷ ለመኾን በቅታለች። በዚህም የክብር ደረጃ ለመቀመጥ ጁሊ ብቸኛዋ ጥቁር ሰዓሊም እንደኾነች እየተነገረላት ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ጁሊ ምሕረቱ ብዙ የማንነት መገለጫዎች ያሏት አርቲስት እየተባለችም ትጠቀሳለች። NBC News ስለርሷ በሰራው ዘገባ ላይ እነኚህን መገለጫዎችን ከሰዓሊነቷ ጋር በማያያዝ የዘገባው ዋነኛ መሰረት አድርጎትነበር። ኢትዮጵያዊት አሜሪካዊት፣ ግማሽ ጥቁር፣ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በጋብቻ የምትኖር፣ እናት፣ እያለ ኤን የማንነቷን መገለጫዎች ዘርዝሯል። የትዳር አጋሯ ጄሲካ ራንኪንም ታዋቂ ሰዓሊ ስትኾን የዚሁ ድፍረት የተባለው አማርኛ ፊልም ሌላዋ ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰርም ነች።

የጁሊ ምሕረቱ አስተዋጽዖ ለፊልሙ ማሰሪያ ገንዘብ በማዋጣት ብቻ የተገደበ አይደለም። አንጀሊና ጁሊ ተሳትፎ እንድታደርግ የጋበዘቻት እና የፊልሙ ዓላማ ግቡን እንዲመታ ትልቅ የማስተዋወቅ ስራ እየሰራች እንደኾነም ቮግ ከተባለው መጽሔት ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ገልጻለች።

የፊልሙን ትኬትና የሚታይባቸውን ከተሞች ዝርዝር እዚህ ይመልከቱ- http://www.difret.com/screenings/