ዋዜማ ራዲዮ- ከሰሞኑ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ቃለምልልስ አድርጓል ። እንደ አንድ የሚዲያ ተቋም የቴሌቭዥን ጣቢያው ይጠቅማል ካለው እንግዳ ጋር ቃለ ምልልስ የማድረግ ሙሉ መብት አለው። ይህን መብት ከማንም ፈቃድ ሊጠይቅበት አይገደድም። ይሁንና ቃለ መጠይቁ የተደረገበት ጊዜና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ከኦሮሞ ህዝባዊ አመፅ ጋር ተያይዞ ያለው የመሪነትና ተምሳሌታዊነት ተደማምረው ጉዳዩን በዝርዝር መመልከት ተገቢ ይመስላል። ጉዳዩ የኦሮሞ ትግል የአስመራን “ወዳጅነት” ደጅ እየጠና ሰለመሆኑ የሚጠቁም አንድምታም አለው። አርጋው አሽኔ የኦሮሞ ትግል ዳግም ወደ አስመራ ማቅናቱ ብርቅ አይደለም፣ ቀድሞ ኦነግ ያደረገውን ዛሬ ወጣቶቹ ሊደግሙት እያሟሟቁ ነው ይለናል። ይህና ሌሎችም መሰናዶዎች ተብራርተው በድምፅ ተሰናድተዋል፣ ከታች ይመልከቱ

በዕለቱ የዋዜማ መፅሄት መሰናዶ
-የኦሮሚያው የኢኮኖሚ አብዮት የት ያደርሳል?
– ቃሊቲ በስቶኮልም
ዋዜማን አድምጡ አጋሩ-