በኢትዮዽያ ታሪክ ውስጥ በአወዛጋቢነታቸው አብይ የሚባሉትን ሶስቱን ይጥቀሱ ቢባሉ የትኞቹን ያነሳሉ? ታሪክ መፃፍም ሆነ ማንበብ ብልሀት ይጠይቃል። የተነገረ የተፃፈ ሁሉ የታሪኩ መጨረሻ ላይሆን ይችላል። ታሪክ በጎም ጎምዛዛም ገፅታ ሊኖረው ይችላል። አንባቢም በሆደ ሰፊነት ካላነበበው ነገሩ ሁሉ እንዳው “ላይ ላዩን” መሆኑ አይቀሬ ነው። በየዘመናቱ የተፈፀሙ “በደሎችን” ለመበየንም ሀላፊነትን ለመውሰድ የሚያበቃ የሞራል ልዕልና ይጠይቃል፣ የታሪክን ዝርዝር-ስራ መገንዘብም አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። ተወያዮቻችን የሚያጋሩትን አድምጡ