Defend Defendersዋዜማ ራዲዮ- ትኩረቱን በምስራቃዊ አፍሪካ ላይ የሚያደርገውዲፌንድ ዲፌንደርስለስደት ስለተዳረጉ የአካባቢው ሃገራት የመብት ተሟጋቾች ያካሄደውን ጥናት ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል፡፡ መቀመጫውን በካምፓላ ዑጋንዳ ያደረገውዲፌንድ ዲፌንደርስ” (ኢስት ኤንድ ሆርን አፍ አፍሪካ ሂዩማን ራይትስ ዲፌንደርስ) በባለ 58 ገጽ ሪፖርቱ፣ በሦሥት ሃገራት ማለትም በኬንያ፣ ዑጋንዳና ርዋንዳ ተጠልለው የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የሙያና ሲቪክ ተቋማት መሪዎችበአጠቃላይ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በስደት እየገፉ ያለውን ሕይወት ቃኝቷል፤ የገጠማቸውን ቀውስና ውጣ ውረድ ፈትሿል፡፡

ዳንኤል ድርሻ ያሰናዳውን ሀኒ ሰለሞን በድምፅ ታቀርበዋለች፣ ያድምጡት አልያም ንባብዎን ይቀጥሉ

መብት በማስከበር ዙሪያ ለአሠርት ዓመታት በእንቅስቃሴ ላይ የቆየውዲፌንድ ዲፌንደርስየሚያተኩርባቸው የቀጠናው አስር ሃገራት ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጂቢቲ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ዑጋንዳ  ርዋንዳ፣ እና ቡሩንዲ ናቸው፡፡  ከጥር እስከ ግንቦት 2016 ዓም ባደረገው ጥናትበአብላጫው በናይሮቢ፣ ካምፓላ እና ኪጋሊ የሚገኙ 50 ስደተኛ የሠብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በአካል አግኝቶ አነጋግሯል፤ ከለላ ከሠጡ ሃገር መንግሥታት መረጃ አሰባስቧል፡፡ በዚሕም የምስራቃዊና አፍሪካ ቀንድ መንግሥታት የሠብዓዊ መብት ረገጣ እየባሰበት መሄዱን ለማሳየት ሞክሯል፡፡

ከሌሎች ስደተኞች ይልቅ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማሕበራት መሪዎችና የመብት ተሟጋቾች በየሃገራቸው ብርቱ ጥቃት እንደሚደርስባቸው፣ በስደትም የደሕንነት ሥጋታቸው ከፍ የሚል መሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ በጥናቱ ቃለ ምልልስ ከተካተቱት መሐል 18 % የሚሆኑት በሃገራቸው አካላዊ ጥቃት ከደረሠባቸው በኋላ ወደ ስደት ማምራታቸውን አስረድተዋል፤ 26 % ከእስር በኋላ አለያም እንዲታሰሩዋራንትመቆረጡን በማወቃቸው፣ 46 % ደግሞ የግድያና መሠል ማስስፈራሪያ ከደረሰባቸው በኋላ ከሃገር መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ አሳዛኙ ጉዳይ ከመብት ተሟጋቾቹ 62 % ያሕሉ ለስደት ከተዳረጉም በኋላ ከአሳዳጆቻቸው በተለያየ መንገድ (ማለትምበአካል፣ በስልክ፣ ኤስኤምኤስ፣ ሶሻል ሚዲያ፣ ሜልወዘተ) ዛቻና ማስፈራሪያው ባሉበት ተከትሏቸዋል፡፡

ከምርጫ ’97 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ መልኩየዛሬ ሁለት ዓመት ስድስት የሚዲያ ተቋማትን በሽብርተኝነት ፈርጃ ያገደችው ኢትዮጵያ 38 ጋዜጠኞችን ወደ ጎረቤት ሃገራት ለስደት በመዳረግ ከሰማሊያ ቀጥላ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች፡፡ አፋኝ የበጎ አድራጎት አዋጅ በማጽደቅ የመብት ተከራካሪዎችን ድምጽ ጸጥ ለማሰኘትም ብዙ ተጉዛለች፡፡ በኤርትራ ለዓመታት የዘለቀው የመብት ጥሰት እንደቀጠለ ነው፡፡ የሱዳኑ ኦማር ሀሰን አልበሽርዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ያወጣብኝን የእስር ዋራንት ደግፈዋልያሏቸውን ተጽዕኖ አሳራፊ መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያድ) ካዘጉ በኋላ በፈላጭ ቆራጭነታቸው ቀጥለዋል፡፡ 2013 ጀምሮ ጋል ቀዝቀዝ በማለት የቀጠለው የደቡብ ሱዳን እርስ በርስ ግጭት ቀውስ የከፋ ሆኗል፡፡ በቡሩንዲ ፒየር ንኩሩንዚዛ ሕገ መንግስት ጥሰው ለሶስተኛ የፕሬዚዳንትነት ዘመን ለመመረጥ በተጓዙበት ሂደት የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎመንግስታቸው የግል ሬዲዮ ጣቢያ እንዲዘጋ፣ የሲቪክ ማሕበራት ቢሮዎች እንዲዘረፍ እና የባንክ አካውንታቸው እንዲታገድ አድርጓል፤ የሶማሊያ ችግር ዘላቂ መፍትሔ አልተገኘለትም፡፡ እነዚህ የየሃገራቱ ችግሮች ደግሞ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማሕበራት መሪዎች በገፍ ስደት እንዲወጡ መግፍዔ ሆኗል፡፡

ከቀጣናው አንጻራዊ መረጋጋት የሚታይባቸው ኬንያ፣ ዑጋንዳና ርዋንዳ የጎረቤቶቻቸውን ስደተኞች ማስጠጋታቸው በመልካም ጎኑ ቢጠቀስምበተለይ የመብት ተሟጋች ስደተኞች በተሠደዱበት ለከባድ ፈተና ተዳርገዋል፡፡ ከደሕንነት ሥጋት እስከ ጤና አገልግሎት እጦት፣ ከሥራ ፈቃድ ማጣት እስክ ፖሊስ ማሳደድ፣ ከምግብ እጦት እስከ ለጎዳና ሕይወት መዳረግ፣ ከግድያ ዛቻ እስከ ታፍኖ መወሰድየስደተኞቹ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ናቸው፡፡

በጥናቱ ከተጠቀሱት መሐልበኦገስት 2014 (በኢትዮጵያ ነሐሴ 2006) ተሠድደው ዲፌንድ ዲፌንደርስድጋፍ ከተደረገላቸው መሐል አንድ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ በመጠለያ እጦት መኖሪያውን የናይሮቢ ጎዳናዎች ለማድረግ መገደዱ ለዚህ አብይ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ስደተኞች በጠበቁት ፍጥነት ለደሕንነታቸው አስተማማኝ ወደሆነ ሶስተኛ ሃገር ዳግም መስፈር አለመቻል ሌላው ችግር ነው፡፡

የዳግም ሠፈራ ሂደት በአማካይ አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ እንደሚወስድ በጥናቱ የተጠቀሰ ይሁን እንጂለሁለት ዓመት በናይሮቢ ከቆዩ 38 ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ጋዜጠኞችወደ ሶስተኛ ሃገር መሻገር የቻሉት የአንድ እጅ ጣቶችን አያሕሉም፡፡ ሌላው ሥጋት ከአሳዳጅደሕንነቶችዒላማ ውጪ አለመሆን ነው፡፡ለደሕንነታቸው ሲባል ስማቸውን ከማንጠቅሳቸውና ቀደም ብለው ከተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች አንዱ  በጃንዋሪ 2014 ዓም መኖሪያ ቤቱ በተመሳሳይ ቁልፍ ተከፍቶውድ ዋጋ ያላቸው ሌሎች ንብረቶቹ ሳይነኩ ላፕቶፑ ብቻ እንደተወሰደበት አስረድቷል፤ ይሕ መሰሉ ክስተት በሶማሊያውያን ጋዜጠኞች ላይም የደረሰ ሲሆን፣ እርምጃው በአሳዳጆቻቸው እንደተወሰደ ይገመታል፡፡    

ለነዚህ ስደተኞች ከለላ የሠጡ መንግሥታት በጸጥታ ሥጋት ሠበብ ስደተኞች በከተማ አካባቢ እንዳይቆዩ ያደርጋሉ፤በከተማ የሚገኙትም የመንቀሳቀስ መብታቸው እንዲገደብ የተደነገገ አዋጅና ያልተጻፈ አሰራር አላቸው፡፡ ከካምፕ ውጪ በዋና ዋና ከተማዎች የሚገኙ ስደተኞች ከአሳዳጅ መንግስቶቻቸው ደሕንነት ዒላማ ለመትረፍ የተሻለ መሆኑን ቢያምኑምበኑሮ ውድነት፣ በፖሊስ ወከባ፣ በሥራ ዕጦት መንገላታት ግን አልቀረላቸውም፡፡ ኬንያስደተኞች የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋልየሚል ደንብ ቢኖራትምመሬት ላይ ያለው ዕውነታ ግን ከዚህ የራቀ ነው፡፡ በሃገሪቱ ፈቃድ ተሰጥቷቸው የሥራ ዕድል ያገኙ ስደተኞች ከሁለት በመቶ አይዘሉም፡፡

ከኬንያና ርዋንዳ የካምፕ ኑሮ አንጻር የተሻለች ናት የምትባለው ዑጋንዳ ስደተኞች ከሃገሬው ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ ትፈቅዳለች፡፡ የቤት መስሪያ እና የግብርና መሬት የሚያገኙበት ዕድል ታመቻቻለችም ተብሏል፡፡ ሆኖም ግን 2006 በጸደቀ አዋጅ ስደተኛው በማናቸውም ዓይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳይሳተፍ ያግዳል፡፡ ወደ ሶስተኛ ሃገር ዳግም የመስፈር (ሪሴትልመንት) ሂደትም በርካታ ዓመታት ይፈጃል፡፡

በስደት የሚገጥሙ ፈታኝ ሁኔታዎች ጋዜጠኞችም ሆኑ የመብት ተሟጋቾች ከመደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዲወጡ የማድረግ ዕድላቸው ሠፊ ነው፡፡ ማለት ግን ውስብስቡን ችግር ተቋቁመው ድምጻቸውን በማሰማቱ የቀጠሉ የሉም ማለት አይደለም፡፡ አፍሪካን ሴንተር ፎር ጀስቲስ ኤንድ ፒስ ስተዲስየተሰኘው ተቋም በዑጋንዳ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የአልበሽር መንግስት ድርጅታቸውን ዘግቶ ከሃገር ያሳደዳቸው አምስት ስደተኛ ሱዳናውያን የመሠረቱት ይሕ ተቋም በአሁኑ ወቅት በሱዳን ጉዳይ ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ በቀዳሚነት ተጠቃሽ መሆን ችሏል፡፡

2010 እዚያው ዑጋንዳ በስደተኞች የተቋቋመውዳርፉር ሪፊዩጂ አሶሴሽን ለአዲስ መጤ ስደተኞች የቴክኒክና ፋይናንስ ድጋፍ ያፈላልጋል፡፡ ካምፓላ የሚኖር አንድ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ዲፌንድ ዲፌንደርስእንደተናገረው ከሆነ ከአፍሪካ ወጥተው ድምጻቸው ቀልጦ ከሚቀር ይልቅ ከቀጠናው ሳይወጡእንዲህ ያለ የሠብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸውን ማጠናከር ይገባል፡፡(የኢትዮፕያውያን ጋዜጠኞች እንቅስቃሴስ ምን ይመስላል. . የሶማሊያና የሱዳን ተጠቅሶ ሲታለፍ የኛዎቹ ምንምእያደረጉ አይደለም የሚል ኢምፕሬሽን እንዳይኖረው፡፡ ለምሳሌ ለውጭ ሚዲያዎች ኮንትሪቢውት ያደርጋል ወይ. . በዚህ መልኩ ቢጠቀስ)

በናይሮቢ የሚኖሩ ሶማሊያውያን ጋዜጠኞች ያቋቋሙት ሶማሊ ኤግዛይልድ ጆርናሊስትስ ኔትወርክ አሶሴሽን” 86 አባላት ያሉት ሲሆን የጋዜጠኞችን ሠቆቃ በመቀነስ ረገድ አብይ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ ማሕበሩ በጦርነት በምትታመሰው ሃገር መሥራት ሳይችሉ አለያም እስርና ጥቃት ሸሽተው ለሚሰደዱ ባልደረቦቻቸው ድጋፍ ያደርጋል፤ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስደተኞች መርጃ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ስለ ጋዜጠኞቹ መረጃ ሲሰጥም ቆይቷል፡፡ አሁን ግን የማይጋፈጡት የሚመስል ችግር ከፊታቸው ተጋርጧል፡፡

የኬንያ መንግስት ከጸጥታ ሥጋት ጋር በተያያዘ የዳዳብ ካምፕን ለመዝጋት መወሰኑ በካምፑ ተጠልለው ለሚገኙ 30 ሶማሊያውያን ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን በናይሮቢ ላሉት ጭምር ሥጋት ደቅኗል፡፡ዳዳብ ከተዘጋ የእኛስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አልተገኘም፡፡ ከካምፑ መዘጋት ውሳኔ በኋላ ናይሮቢ የደረሱ ስደተኛ የሶማሊያ ጋዜጠኞች ምዝገባ ማድረግ እንኳ አልቻሉም፤ ዩኤንኤችሲአር ምዝገባ ቢጀምር እንኳ ከዚህ በኋላ የሚመዘገቡ ስደተኞችየመጀመሪያ ቃለ ምልልስ ለማድረግ በትንሹ የሁለት ዓመት ቀጠሮ የሚሰጣቸው መሆኑ ሁኔታውን ይበልጥ ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ 

በኬንያ ከተጠለሉ 600 ሺህ የማያንሱ ስደተኞች ውስጥ 63 ሺህ ያሕሉ በናይሮቢ ከተማ ይኖራሉ፡፡ 253 ሺህ የቡሩንዲ ስደተኞች መሐል 75 ሺህ ያሕሉ በርዋንዳ ተገን ጠይቀዋል፡፡ በኪጋሊ ከተማ ከሚኖሩ 25 ሺህ ስደተኞች ውስጥ 24 ሺህ 500 የርዋንዳ ዜጎች ናቸው፡፡ ስደተኛን በመቀበል ከአሕጉሪቱ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ዑጋንዳ 525 ሺህ ስደተኞች ያስተናገደች ሲሆን፣ 76 ሺህ ያሕሉ በርዕሰ መዲናዋ ካምፓላ ይኖራሉ፡፡