Women affected by drought around Warder Somali region
Women affected by drought around Warder Somali region

ዋዜማ ራዲዮ- ለረሀብ ለተጋለጡ ወገኖች ለመድረስ በምናደርገው ጥረት የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት እየፈጠሩና እገዳ እየጣሉ አላሰራን ብለዋል ሲሉ ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች አቤቱታ አቀረቡ።
የመንግስታቱ ድርጅትን ጨምሮ ከሰላሳ በላይ ድርጅቶች ለጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አቤቱታቸውን ማድረሳቸውን አንድ የረድዔት ድርጅት ሀላፊ ለዋዜማ ገልፀዋል።
በሀገሪቱ የድርቅ አደጋ ከተባባሰበት ካለፉት አራት ወራት ወዲህ በለጋሽ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ክልከላዎች በመጣላቸው አስቸኳይ እርዳታ በወቅቱ ማድረስ አለመቻሉን ድርጅቶቹ ይናገራሉ። በድምፅ የተሰናዳ ዝርዝር አለን፣ ከታች

“ለመገናኛ ብዙሀን ያለመንግስት ፈቃድ መግለጫ እንዳንስጥ ተከልክለናል፣ እገዳውን ጥሰን መግለጫ በመስጠታችንም ዛቻና መስፈራሪያ ደርሶብናል”  እንደ ሀላፊዎቹ ገለፃ።
በተለይ በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በሞት አፋፍ ላይ ላሉ ተጎጂዎች እርዳታ ማድረስ ባለመቻሉ አስቃቂ አደጋ እየደረሰ ነው ብለዋል አንድ የእንግሊዝ የረድዔት ድርጅት ሀላፊ።

ሁኔታው በመባባሱና የሚፈለገው እርዳታ ሊገኝ ባለመቻሉ የረድዔት ድርጅቶቹ ሀገር አቀፍ አስተባባሪዎች ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ስጋታቸውን ተናግረው አለማቀፍ እርዳታ እንዲገኝ ተማፅኖ አቅርበዋል።
አሁን በመንግስት እጅ ያለው የእርዳታ መጠን ከሶስት ሳምንት ያልበለጠ ጊዜ የሚያቆይ መሆኑንና እርዳታ ባይገኝ መንግስት በራሱ በጀት የእርዳታ እህል ገዝቶ እንደሚያቀርብ ተናግሯል።
ይሁንና የእርዳታ እህል ገዝቶ ለማቅረብ ቢያንስ ሁለት ወራት የሚፈጅ በመሆኑ የበርካታ ስዎች ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ፍርሀት እንዳላቸው ለጋሾቹ እየተናገሩ ነው።
” የተያዘው አቋም የሀገር ገፅታ ከሚበላሽ የተከፈለው መስዋዕትነት ተከክሎ የረሀቡ ጊዜ ያልፋል የሚል መሆኑንና ይህም ፈፅሞ ስብዓዊነት የጎደለው በመሆኑና የሚያስጠይቅም በመሆኑ ለጉዳዩ አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡበት ጠይቀናቸዋል”

“ኢትዮጵያ በልማት ጥሩ ውጤት ማስመዝገቧን መላው አለም ያውቃል፣ በተመሳሳይ የረሀብ አደጋውን መደበቅም ሆነ ማሳነስ የሚቻል አይመስለኝም”  ይላሉ በሶማሌ ክልል ከመስክ ስራቸው ላይ በፖሊስ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ የዓለማቀፍ ድርጅት ስራተኛ።

በህፃናት መመገቢያና ማገገሚያ ጣቢያዎች እንዲሁም ችግሩ በተባባሰባቸው አካባቢዎች ፎቶ ማንሳት ለጋዜጠኞች መረጃ መስጠት በጥብቅ የሚከለለል ሲሆን በየጣቢያዎቹ መንግስት የራሱን ጆሮ ጠቢዎች አስቀምጦ የረድዔት ሰራተ ኞች ማንንም እንዳያምኑ እየተደረገ ነው።
አሁን በሀገሪቱ ስምንት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋሉ። በድምፅ የተሰናዳ ዝርዝር አለን፣ ከታች

https://youtu.be/H8H_oe4W5XM