ethio telecomዋዜማ ራዲዮ፡ ኢትዮ-ቴሌኮም በቢሊየን ዶላር ሊያካሂድ የነበረውን ሶስተኛ ዙር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሰረዘ።
የድርጅቱ የቅርብ ምንጮች እንደነገሩን ይህ ሶስተኛ ዙር የማስፋፊያ ፕሮጀክት በሀገሪቱ መቶ ሚሊየን የሞባይል ኔትወርክ መሽከም የሚችል እቅም የማድረስ ዕቅድ የነበረው ነው። እንዲሁም አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅት ሲያደርግ ነበር።
ይሁንና በቅርቡ መንግስት በዘርፉ የግል ባለሀብቶች በአነስተኛ ድርሻ እንዲሳተፉና ሀብታቸውን እንዲያፈሱ ካወጣው እቅድ ጋር ተያይዞ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በመንግስት በጀት መከናወኑ እንዲሰረዝ ተደርጓል።
ፕሮጀክቱ ምናልባትም አዳዲስ አክሲዮን የሚገዙ የግል ኩባንያዎች እንዲያከናውኑት ሊተው እንደሚችል ጉዳዩን የሚያውቁ ያስረዳሉ።
ሁዋዊ ፣ዜድቲኢ እና ሶኒኤሪክሰን የተባሉት አለማቀፍ ኩባንያዎች የሶስተኛውን ዙር ማስፋፊያ ለማከናወን ከተመረጡት መካከል ነበሩ።
ይሁንና ኢትዮ-ቴሌኮም ከዚህ ቀደም ያለበትን 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ዕዳ በዶላር መክፈል አልቻለም። ኢትዮ-ቴሌኮም ብድሩን የወሰደው በመንግስት ዋስትና ነው። ይህም የሀገሪቱን ዕዳ ካናሩት ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። ሁለተኛው ኢትዮ-ቴሌኮም የኔትወርክ ማስፋፊያ ማስፋፊያ 1ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ወወጥቶበታል። አንደኛው ማስፋፊያ  1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ተደርጓል። የሶስተኛው ዙር ማስፋፊያ የገንዘብ ትመና ከአለማቀፍ      ኩባንያዎች እንዲቀርብ እየተጠበቀ ነበር። አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊየን ያህል ይገመታል።

ከሶስተኛው ማስፋፊያ መሰረዝ ተከትሎ ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የእሴት ቆጠራ በማድረግ ራሱን ከሚመጡ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚሰራበትን ስነድ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።