መንግስት የግል ተቋማት ሰራተኞችን የጡረታ ገንዘብ ወደራሱ ካዝና ማዛወር የፈለገው ለምን ይሆን?

 

Bankሰሞኑን አዲሱን የግል ተቋማት ሰራተኞችን ጡረታ ረቂቅ አዋጅ ተከትሎ ገንዘባችን ሊወሰድብን ይችላል ብለው የስጉ ስራተኞች ገንዘባቸውን ከባንክ እያወጡ ነው። ሌሎች አሰሪዎቻቸውን እየጎተጎቱ ይገኛሉ። ዘጋቢያችን ፍሬስብሀት ስዩም የላከችልንን ዘገባ ቻላቸው ታደሰ ያቀርበዋል። አድምጡት

በፕሮቪደንት ፈንድ የታቀፉ የግል ድርጅት ሠራተኞችን በመንግሥት በሚተዳደረው የግል ድርጅቶች ጡረታ እንዲዘዋወሩ የሚያስገድድ ማሻሻያ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ፣ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች በባንኮች የስቀመጡትን ገንዘብ ለማወጣት ሲጣደፉ ይህ ሪፖርተር ታዝቧል ፣ ባንኮችም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ከተለመደው ውጪ ገንዘብ መሚያወጡ ደንበኞቻቸው ተጨናንቀው ይታያሉ። ባለፈው ግንቦት ወር የቀረበው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በፕሮቪደንት ፈንድ ታቅፈው የነበሩ የግል ድርጅት ሠራተኞችን ሙሉ በሙሉ ወደ የግል ድርጅቶች ጡረታ እንዲገቡ የሚያስገድድ ነው፡፡

የተያዘው የሰኔ ወር የመጨረሻ የሥልጣን ዘመኑ የሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ አጭር ውይይት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ዝንዲሁም ለሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በጋራ ለዝርዝር ዕይታ እንደመራው የታወሳል፡፡ አዋጁ የተመራላቸው ቋሚ ኮሚቴዎችም የህዝብ ይውይይት መድረክ በመጥራት ከግል ድርጅቶች አሰሪዎች እንዲሆም ከተጋበዙ የግል ሠራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት አብዛኞቹ ተሳታፊዎች አዋጁን አበክረው ተቃውመዋል፡፡ የስራተኞቹ ተቀውሞ የበረታበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል ድርጅቶች የጡረታ ፕሮግራሙ በስራተኞች ስምምነት ላይ የተመሰረተ እንጂ ግዴታ እንደሌለበት ጠቁሟል።

የሰራተኛ ተወካዮቹ ግን ፕሮግራሙ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ ህጉ በቂ ማረጋገጫ አይሰጥም፣ በስምምነት ነው የሚለው መከራከሪያም ተቃውሞ ሲበረታ የመጣ ነው በማለት ተከራክረዋል። ከአራት አመት በፊት የጸድቆ አሁን በተግባር ላይ ያለው የግል ድርጅት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ማሻሻያ ከያዛቸው ነጥቦች መካከል የግል ድርጅት ሰራተኞች አጠቃላይ ፕሮቪደንት ፈንድ እንደያዙ በጡረታ ይሸፈኑ የሚለው ይገኝበታል።

በቅርቡ ይህን አዋጅ ለማሻሻል ተብሎ የቀረበው ረቂቅ ግን ሠራተኞች፣ ከፕሮቪደንት ፈንድና ከጡረታ ዐቅድ እንዲመርጡ የሰጣቸውን ነጻነት የሚነጥቅ ነው ሲሉ የህግ ባለሙያዎች እየተቹት ነው፡፡

መንግስት ቀደም ሲል የወጣውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት የተለያዮ የትርጉም ክፍተቶች በመኖራቸው በአሰራር የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ነው ሲል በአዋጁ አባሪ ገፅ አብራርቷል። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች መንግስትት በየቦታው ለ መራቸው በቢልየን ዶላር የሚጠይቁ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በቂ ገንዘብ ማሰባሰብ ባለመቻሉ፣ ለፕሮጀክት መደጎሚያ የሰራተኞችን የጡረታ አገልግሎት አበል ወደካዝናው ለማሸጋገር የቀየሰው ስልት ነው ይላሉ። እንዳውም አንዳንድ ሰራተኞች አዋጁ የቀረበበትን ጊዜ ተንተርሰው መንግስት ክህደት ፈፅሞብናል ሲሉ ተደምጠዋል፣ ምክንያቱንም ሲናገሩ ኢህ አዴግ በምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ በማግስቱ አዋጁን ወደ ፓርላማ ያመጣው ከቅን መንፈስ በመነጨ እንዳልሆነ ፍንጭ ይሰጣል።

ለበርካታ አመታት በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ የቆጠቡ የግል ድርጅት ሰራተኞች መንግሥት የፕሮቪደንት ፈንድ ገንዘባችውን ወደ ካዝናው ከማጠቃላሉ በፊት በሚል ፍራቻ አሠሪዎቻቸው እንዲሰጧቸው በመጠየቅ ላይ ያሉ ሠራተኞች ሲኖሩ አንዳንዶቹ ድግሞ ተፈቅዶላቸው እያወጡ እንደሆን ተገንዝበናል እንዲሁም የኩባንያ ባለቤቶች ወይም ባለ ብቶች በርካታ የማኅበራዊ ዋስትና አማራጮች እንዳሏቸው፣ ከእነዚህም መካከል የጡረታ ኢንሹራንስ ሊገዙ እንደሚችሉ እየታወቀ፣ መንግሥት የራሱ ተጧሪ ሊያደርጋቸው መፈለጉ አስገራሚ እንደሆነባቸውም የገለጹ አልታጡም፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የግል ድርጅት ማለት በኢትዮጵያውያን ብቻ የተያዘ አለመሆኑንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ያቋቋማቸው ኩባንያዎችም እንዳሉ የሚገልጹት ተቺዎች፣ እነዚህ የውጭ ዜጎች በአገራችው የተሻለ የማኅበራዊ ዋስትና ሽፋን የሚያገኙ ሆነው ሳለ መንግሥት እነዚህንም ተጧሪ ለማድረግ ማሰቡ እንዳስገርማቸውም ይገልጻሉ፡፡ በዚሁ መሠረት የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የነበረ ሠራተኛ በሙሉ ወደ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ዐቅድ የሚገባ ሲሆን፣ ፈንዱና ሠራተኛው ያገለገለው ዘመን ግንዛቤ እየገባ ወደ ግል ጡረታ ኤ ንሲ ፈንዱ የሚዘዋወር ይሆናል፡፡

በዚህም መሰረት ረቂቅ አዋጁ ከፀደቀ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተፈጻሚነት የነበረው የፕሮቪደንት ፈንድ ሥርዓት ይቋረጣል፡፡ የፕሮቪደንት ፈንድ ሥርዓት ሊቀጥል የሚችለው የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይም ኢ-­‐መደበኛ በሆኑ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ድርጅቶች በግል ጡረታ ዐቅድ ላለመሳተፍ ከወሰኑና ሠራተኞቻቸውን የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ካደረጉ ነው፡፡