Dawd Ibssa-OLF chair- FILE

ዋዜማ ራዲዮ- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንጃዎች ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ስጥቶ እንዲመዘግባቸው ማመልከቻ ማስገባታቸውን ዋዜማ ራዲዮ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

አመልካቾቹ በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግና በቅርቡ ከድርጅቱ ያፈነገጡ ግለሰቦች የተካተቱበት አዲስ የተመሰረተው ኦነግ ናቸው።

አሁን የተመሰረተው ኦነግ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ በሶደሬ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል። በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በበኩሉ ጠቅላላ ጉባዔውን አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ በሚገኘው ፅህፈት ቤቱ አድርጓል።


የክፍፍሉ ምክንያት የስልጣን ይገባኛልና የውስጠ ድርጅት ዲሞክራሲ ማጣት መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ያስረዳሉ።
ኦነግ ለክፍፍልና ለአንጃ አዲስ አይደለም። በተለያየ ጊዜ ድርጅቱ በገጠመው መሰንጠቅ እስከአሁን ስምንት ያህል ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል። አሁን ቢያንስ ስድስቱ ሀገርቤት ገብተው በፖለቲካ መድረኩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር የድምፅ መረጃ ከታች ይመልከቱ

https://youtu.be/ZkwFgrx4N7Y