ከስድስት መቶ ቀናት በኋላ በፍርድ ቤት ነፃ ተብለው የተፈቱት ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ ከእስር ቤት ከወጡ ከሰዓታት በኋላ በድጋሚ ታሰሩ። ሁለቱ ወጣቶች በነ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ የክስ መዝገብ የኢንተርኔት ደህንነት ስልጠና ለመውሰድ በማመልከታቸው “የሽብር ስልጠና ወስደዋል” በሚል ተከሰው 647 ቀናት እስር ቤት አሳልፈዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፍርድ ቤት በነፃ እንዲለቀቁ ያሰናበታቸው ሲሆን ዛሬ ሰኞ ከቂሊንጦ እስር ቤት እንደወጡ በድጋሚ ታስረው ወደ ማዕከላዊ ተወስደዋል። የታሰሩበትን ምክንያት አልተገለፀም።