[Wazema Alerts] የኢትዮዽያ መንግስት ለሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት መስጠት አቆመ። የግብርና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በዘርፉ የሚጠበቀው ዉጤት ሊገኝ ስላልቻለ ለተወሰነ ጊዜ መሬት መስጠት ቆሟል። ኤጀንሲው ሶስት ሚሊየን ሄክታር መሬት ከክልሎች አሰባስቦ ለባለሀብቶች ሲያድል እንደነበረ ይታወቃል። ድርጅቱ እንደገለፀው መሬት ከወሰዱት ዉስጥ ወደ ስራ የገቡት ከሰላሳ በመቶ አይበልጡም። ከፍተኛ የፋይናንስ ማጭበርበርም በዘርፉ ታይቷል።
መንግስት በኦሮሚያ የተከሰተው አይነት ተቃውሞ በመስጋት የመሬት እደላውን ሳያቆም እንዳልቀረ ምንጮች ይገልፃሉ። በዘርፉ ይህ ነው የሚባል ውጤት አለመገኘቱም ሌላው ምክንያት ነው።