trump[Wazema Alerts] የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ለአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ ስልክ ደወሉ። ኪር ለዶናልድ ትራምፕ መልካም ምኞታቸውን የገለፁ ሲሆን በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ድል እንዲቀናቸው ተመኝተዋል። ትራምፕ ከተመረጡ ዳጎስ ያለ የኢንቨስትመንት ፍስት ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚኖር ያላቸውም ተሰፋም ኪር ተናግረዋል ሲል ሱዳን ትሪብዩን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ትራምፕ በበኩላቸው ፈፅሞ ካልጠበቁት አፍሪካዊ ሀገር የስልክ ጥሪ መቀበላቸውንና መደነቃቸውን ተናግረዋል። ትራምፕ አፍሪቃ አሜሪካውያንን የሚያጥላላና ዘረኛ ቅስቀሳ በማድረግ ይታወቃሉ።