Month: September 2015

የመተካካቱ ቅርቃር

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በዚህ አመት አገባድደዋለሁ ያለው የአመራር መተካካት ቅርቃር ውስጥ ገብቷል። ከጅምሩ መተካካት የሚለው ሀሳብ ለረጅም ጊዜ በስልጣን መቆየት ከሚያስከትለው ወቀሳ ለመዳን የተዘየደ እንጂ ከልብ የታሰበበት አልነበረም ይላሉ ተወያዮቻችን።…

ሀበሻ በአሜሪካ- እየተቀየሩ ያሉ እውነታዎችና የኢኮኖሚ ፈተናው

እየተቀየረ ባለው የአለም ኢኮኖሚ በውጪ በተለይም በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን አዲሱን የኢኮኖሚ ፈተና እንዴት ሊወጡት ይችላሉ የሚለው መወያያ ርዕስ ወቅታዊ ይመስላል። በርካት ወገኖች የተሰማሩበት የታክሲ ትራንስፖርት የስራ ዘርፍ አዳዲስ ተግዳሮቶች…

ኢህአዴግ ውህደትን ይፈራል

የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ኢህአዴግ የብሔር ውክልናን ያለቀቀ አንድ ፓርቲ ለመሆን ተሳነው በህወሀትና በሌሎቹ ፓርቲዎች መካከል የጌታና ሎሌ ግንኙነት ከመኖሩ ባሻገር ፓርቲው ውስጣዊ ሽኩቻና ውጥረት በዚሁ ከቀጠለ አደጋው የከፋ ስለመሆኑ…

የዻዻሱ የቀልድ ዘመቻ

የካቶሊኩ ዻዻስ ፖፕ ፍራንሲስ የቤተክርስቲያኒቱ አማኞች ከአቅም በላይ ከሆነ ፍቺ መፈፀም “ከፈጣሪ አያጣላም” ሲሉ መናገራቸው የሰሞኑ ትልቅ ዜና ነበር። “ድመትና ውሻ ከማሳደግ – ውለዱ ክበዱ ራስ ወዳድ አትሁኑ” ሲሉም መክረዋል።…

መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር…… (ክፍል ሶስት)

የመለስን ሞት ተከትሎ መጪው ጊዜ ለገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የተደበላለቀ ሥዕልን ያሳያል። የፓርቲው አመራሮች ግን በፓርቲው ውስጥ ያተጋረጡ ስጋቶችን በመሸፋፈን በጥገናዊና እርባና በሌለው ግምገማ “እየፈታነው ነው” የሚል ስዕል በአባለቱና በህዝቡ ዘንድ…

የኢህአዴግ ‘ማዕከላዊ ዴሞክራሲያዊነት’ ከህዋስ እስከ ድርጅታዊ ጉባዔ!

ዴሞክራሲ ማዕከላዊነት የጥቂቶችን ሀሳብ በብዙሀኑ ላይ በመጫን ይሁንታ ለማግኘት አምባገነን አገዛዝ የሚጠቀምበት መሳሪያ ሆኗል። ኢህ አዴግም የዚህ ሰለባ ሲሆን የፓርቲ ስልጣንን ለማስጠበቅ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ በጥቂቶች ሀሳብ ላይ እንዲንጠለጠል ያደርገዋል…

ኤርትራና አሜሪካ፡ ፍቅር እንደገና?

ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማግስት ሆድና ጀርባ የሆኑት አሜሪካና ኤርትራ በተለያየ መንገድ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጮች መታየት ጀምረዋል። ኤርትራ በሶስተኛ ወገን በኩል ፍለጎቷን ብትገልፅም አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት አቋም…

ኢህአዴግ ስንት ነው?

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከማለዳው አፈጣጠሩ በአንድነት ሳይሆን በልዩነት ላይ የተመሰረተና ቆሜለታለሁ የሚለውን የብሄር መብት እንኳን በቅጡ የማያከብር ስለመሆኑ የፓርቲውን የውስጥ አሰራር የሚያውቁ ያስረዳሉ። ይህም ፓርቲውን የመሰረቱት ጥምር ፓርቲዎች ከትብብር ይልቅ…