Month: July 2015

“ጦርነቱ”

የአርበኞች ግንቦት 7 አማፅያን በኢትዮዽያ መንግስት ላይ ጥቃት መጀመራቸውን    አስታውቀዋል። መንግስት ጣቱን ወደ ኤርትራ ቀስሯል። ፍጥጫው ክፍለ አህጉራዊ ቀውሱን  ሊያባብሰው ይችላል የሚለው ስጋት ከፍተኛ ነው። ይህን የሶስትዮሽ ፍጥጫ  ተመልክተነዋል።ያድምጡት…

የሃኪንግ ቲም መጠለፍ የኢትዮዽያን የስለላ አቅም ይገታው ይሆን?

በቅርቡ ለኮምፒውተር ስለላ የሚውል ቴክኖሎጂ ሲያቀርብ የነበረው ሀኪንግ ቲም የራሱና የደንበኞቹ ሚስጥር ከተጋለጠ በኋላ የተማርናቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ። መዝገቡ ሀይሉ ቢታሰብባቸው ያላቸውን የሀኪንግ ቲምን መረጃ ተንተርሶ ይነግራችኋል። አድምጡት

ሰላማዊ የትግል አማራጭ አበቃለት? ውይይት ክፍል ሁለት

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በዛሬይቱ ኢትዮዽያ ያስፈልጋሉን? ተቃዋሚዎች ከድራማዊው የኢህአዴግ መቶ ፐርሰንት የምርጫ ውጤት በኋላ ዳግም ሰለምርጫ ወንበር ሊታገሉ ይገባልን? ይቻላቸዋልስ? ተወያዮቻችን የተለየ ሀሳብ አላቸው። ውይይቱን ያድምጡ የመጀመሪያው ክፍል ውይይትን እዚህ ያድምጡ…

Wazema Alerts- በፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ወቅት የሽብር ጥቃት እቅድ አለ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የምስራቅ አፍሪቃ ጉብኝት ወቅት የሽብር ጥቃት ለማካሄድ የተያዘ ሴራ መኖሩን የዋሽንግተን የደህንነት ምንጮች አመለከቱ። አሜሪካ ዜጎቿ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ ከተቻለም ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት አካባቢ ዝር እንዳይሉ…

“የኢትዮዽያ የብየነ መረብ ደህንነት ተቋም INSA ገልቱ መስሪያቤት ነው “

የኢትዮዽያ የብየነ መረብ ደህንነት ተቋም ወይም በፈረንጁ ቃል INSA ገልቱ መስሪያቤት ነው ሲል የራሱ የስለላ ሸሪክ ወነጀለው። ኢንሳ የኢሳት (ESAT) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነዐምን ዘለቀን ለማጥመድ ብዙ መድከሙን የሚጠቁም መረጃ ይፋ…

ወደብ አልባ መሆን ስንት እያስከፈለን ነው? (ሪፖርት ክፍል ሁለት)

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የፖለቲካ ኪሳራውን በመፍራት ይመስላል ሀገሪቱ ወደብ አልባ በመሆኗ በአጠቃላይ እየደረሰ ስላለው ብርቱ ኢኮኖሚያዊይና ማህበራዊ ቀውስ ይፋ ማድረግ የማይደፍረው። አሁን አሁን ግን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናት፣…

ኢትዮዽያ የልውጥ ህያዋን (GMO) በሀገሪቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ህጓን አላላች

ኢትዮዽያ የልውጥ ህያዋን (GMO) በሀገሪቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ህጓን አላልታለች። የህጉ መሻሻል አደገኛና የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም የሚጎዳ ነው ይላሉ የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች። መንግስት በለገሾች ተፅዕኖ ህጉን ለማሻሻል መገደዱን የሚያስረዱም አሉ።የፍሬስብሀት…

BREAKING NEWS- አምስት ጦማርያንና ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ

  ዋዜማ ሬድዮ/UPDATED/– የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ጋዜጠኞቹ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ እና አስማማው ሃይለጊዮርጊስ ከእስር ተፈቱ።ኤዶምና ማህሌት በይፋ ከቃሊቲ እስር ቤት የሚወጡት ነገ ማለዳ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ዛሬ ማምሻውን…