የፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ የሚሊዮን ዶላር ፈተና
እኛን የሚገደንን ማን ከቁብ ይቆጥረዋል? የኛን ታሪክ ማን ይተርክልናል? ሌላው ዓለም ስለራሱ የሚነግረንን በሲኒማውም በሙዚቃውም እኛጋ ሲያደርስ ስለራሳችን የምንለው በጣም ጥቂት ነው። ኃይሌ ገሪማን የመሰሉ ጥቂት ብርቅዬ የፊልም ባለሞያዎች ይህን በመለወጥ እኛም የምንለው እንዳለን ለማሳየት እየጣሩ ነው። ፈተናው ግን ቀላል አይደለም። ኃይሌ ገሪማ እስከዛሬ ሰርቶ ባሳያቸው ፊልሞቹ ተወዳጅነትን አትርፏል። አሁን አዲስ ሊሰራው ላቀደው ፊልም የሚውል አዲስ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በድረገጽ ጀምሮ የፊልም አፍቃርያንን አብረን እንስራ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።ይህን የድረገጽ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በተመለከተ መዝገቡ ኃይሉ የሚከተለውን አዘጋጅቷል።