ዋዜማ ራዲዮ- በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው ፀረ አገዛዝ ህዝባዊ ተቃውሞና እያስከተለ ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል። ህዝባዊ ተቃውሞዎቹ የራሳቸው የሆነ ሀገራዊም አካባቢያዊም ገፅታ አላቸው። በኦሮሚያ የተከሰተው ተቃውሞ ጋል ረገብ እያለ አሁንም ድረስ ቀጥሏል፣ በጎንደር የተቀሰቀሰው ተቃውሞም ቢሆን የመንግስትን የፀጥታ ሀይሎች የተገዳደረ ነበር። በኮንሶና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ነበሩ። ከነዚህ ተቃውሞዎች የኦሮሚያና የጎንደሩን እንደ አብነት አንስተን አንዱ ከሌላው በምን ይለያል? ብለን ተመልክተነዋል። አርጋው አሽኔ ያሰናዳውን ዘገባ እነሆ