ebcየኢትዮዽያ ቴሌቭዥን (Ethiopia Broadcasting Corporation) ሃምሳኛ የልደት በዓሉን ለማክበር እየተሰናዳ ነው። ይህ አንጋፋ ሚዲያ በአፍሪቃ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደብ ቢሆንም ባለፉት ሶስት መንግስታት የስርዓቶቹ አገልጋይ እንጂ የህዝብን ይሁንታ ለማግኘት አልታደለም።

ተቋሙ የልደት በዓሉን በ10 ሚሊያን ብር እንዲያዘጋጅለት የግል ድርጅት ቀጥሯል። ስለምን አንጋፋው ድርጅት ልደቱን በራሱ ማዘጋጀት ተሳነው? ከፓለቲካ መገልገያነቱ ባሻገር አሁን አሁን በሙስና የሚታማው የኢትዮዽያ ቴሌቭዥን ያለፉትን ዓመታት ጉዞ በጨረፍታ ተመልክተነዋል። አርጋው አሽኔ ያዘጋጀውን አድምጡ