በቅርቡ ራስን የማስተዳደር መብት የተፈቀደለት የቅማንት ብሄረሰብ ከጠየኩት 126 ቀበሌ 52 ቀበሌ ብቻ ነው የተፈቀደለኝ፣ ቀሪዎቹ 74 ቀበሌዎች ይሰጡኝ ሲል ብርቱ ተቃውሞ አቅርቧል። ለቅማንት ብሄረሰብ ራስን የማስተዳደር መብት መፈቀዱን ተከትሎ ሌሎች ብሄረሰቦችም በውሳኔው በመነቃቃት ነባርና አዲስ የማንነቴ ይታወቅልኝ፣ ራሴን ማስተዳደር ይፈቀድልኝ የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው። ጉዳዩ ለአወዛጋቢው የኢትዮዽያ የብሄር ፌደራሊዝም አዲስ ፈተና የሆነ ይመስላል። የሪፖርተራችንን ዘገባ አድምጡ