Daniel Bekele, Head of EHRC- Photo- Reporter

ዋዜማየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮበአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮችእጅግ አሳሳቢኾነዋል ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኢሰመኮ፣የትጥቅ ግጭቱ ወደ ክልሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች መስፋፋቱን ካሰባሰበው መረጃ መረዳቱን ገልጧል።

ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 30 2015 ዓ፣ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ፣ በሰሜን ጎጃም ዞን አዴትና መራዊ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞንደልጊ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢትና አንጾኪያ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው ባንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች በግጭቱ በርካታ ሲቪል ሰዎች መሞታቸውን ኢሰመኮ ገልጧል። 

ኢሰመኮ፣ ከሐምሌ 24 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2015.ም በአዴት፣ ደብረማረቆስ፣ ደብረታቦር፣ ጅጋ፣ ለሚ፣ ማጀቴ፣ መራዊ፣ መርጦ ለማርያምና ሸዋ ሮቢት ከተሞች ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ የተያዙ ሰዎችመንገድ ላይ የተገኙና ያልታጠቁ ሰዎችጦር መሣሪያ ደብቃችኋል የተባሉ ሰዎችየሰዓት እላፊ ገደቦችን ተላልፈው የተገኙ ሲቪል ሰዎችእናበቁጥጥር ስር የዋሉየፋኖ አባላት ከሕግ ውጭ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል ብሏል። በዚኹ ድርጊት ላይ የኢሰመኮና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ ምርመራ አስፈላጊ መኾኑንም መግለጫው አመልክቷል። 

የኢሰመኮ መግለጫ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማዕከላዊ ዕዝ በይፋ ከገለጠው ውጭ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎችና አዲስ አበባና ሸገር ከተሞችየተስፋፋና የዘፈቀደ እስርእንደተፈጸመም ገልጧል። 

በደቡብ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ግቢ ገና ቁጥራቸው ያልታወቀ ታሳሪዎች እንደሚገኙ የገለጠው ኢሰመኮ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ በሚገኝ ጊዜያዊ ማቆያ ሕፃናት፣ ሴቶችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ታስረው እንደነበርና በማዕከሉ የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ማረጋገጡንም አመልክቷል። [ዋዜማ ]