Tag: Amhara

የአዲስ አበባ ጉዳይ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ የሚካሄደውን ምክክር ጥላ አጥሎበታል

ዋዜማ- ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ25ኛ ቀን ውሎው በሥራ ቡድን ደረጃ የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ላይ መመካከር ጀምሯል። ሀሙስ ሐምሌ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ለሥራ ቡድን ጉባኤዎች የቀረቡ የስልታዊ ቡድን ምክረ ሀሳቦችን…

በክልል ያሉ የጤና ባለሙያዎች ቃል የተገባልን ክፍያ መተግበር አልቻለም ሲሉ አቤቱታ አሰሙ

ኦሮሚያ በአስቸኳይ እንዲከፈላቸው አዟል፣ አማራ በጀት የለኝም ብሏል ዋዜማ- የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ 12 ጥያቄዎችን ይዘው በሥራ ማቆም አድማ የተደገፈ እንቅስቃሴ ካደረጉ በኋላ መንግሥት ችግሩን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መስማማቱ…

የዋግኽምራ ወረዳዎች በትግራይ እና በአገው ሃይሎች ቁጥጥር ስር

ዋዜማ- በትግራይ ሃይሎች እና በአገው ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ቁጥጥር ስር ያሉት የዋግኽምራ ዞን ሁለት ወረዳዎች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ ምግብ እና መድሃኒቶችን ጨምሮ መሰረታዊ የሚባሉ ቁሳቁሶች እንዳይገቡ በመደረጋቸው እንዲሁም የባንክ እና…

የሀገራዊ ምክክር ኮምሽኑ አራት አብይ ፈተናዎች ገጥመውኛል አለ

ዋዜማ- በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የመፍጠር ራዕይ የሰነቀው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አራት የጎሉ ፈተናዎች ገጥመውኛል ብሏል። በተቋቋመበት አዋጅ የሦስት ዓመት ዕድሜ ተሰጥቶት የነበረው የምክክር ኮሚሽን፤ የተሰጠውን የአንድ ዓመት…

በአማራና በትግራይ ተፈናቃዮች “ተርበናል” እያሉ ነው

መንግስት ዕርዳታ እያቀረብኩ ነው ብሏል ዋዜማ – የኢትዮጵያ መንግስት ከዕርዳታ ጥገኝነት ለመውጣት ዘመቻ በጀመረበት፣ የአሜሪካ መንግስት ከፍ ያለ የገንዘብ ድጋፍ ባቋረጠበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች የረሀብ ፈተና…

እገታ ፣ግድያና የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በራያ አወዛጋቢ አካባቢዎች

ዋዜማ- በአማራና በትግራይ ክልል የይገባኛል ውዝግብ ባለበት የራያ አካባቢ እገታ፣ ዝርፊያና ግድያ እየተስፋፋ መሆኑንና ወጣቶችን አስገድዶ ለውትድርና መመልመልም እየተበራከተ መምጣቱን ዋዜማ ካሰባሰበችው መረጃ ማረጋገጥ ችላለች።  ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው…

የሸዋሮቢት ከተማ የፀጥታ ሀላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ

ዋዜማ- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለማ ወንድአፈረው ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮች ስምታለች። የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ኃላፊዎች…

በአዲስ አበባ “የሻዕቢያ ተልዕኮ አስፈፃሚ” ናቸው የተባሉ 224 ስዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ዋዜማ- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ 224 “የሻዕቢያ መንግሥት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች” ናቸው ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ዋዜማ ከፀጥታና ደህንነት ምንጮች ስምታለች። ቢሮው፣…