Category: Current Affairs

መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ በግዳጅ ለሚመለሱ ዜጎች 90 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እፈልጋለሁ አለ

ዋዜማ ራዲዮ- ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ ዜጎችን በራሴ አቅም ተቀብዬ አቋቁማቸዋለሁ ሲል የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ከለጋሾች 90 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ካልተገኘ ስራውን ለማከናወን እንደሚቸገር አስታወቀ። የሳውዲ አረብያ መንግስት ህገ ውጥ የሆኑ የውጭ…

በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል ነፋስ ገብቷል

ጣልቃ ገብነታችሁን አቁሙልኝ የሚሉ ቅሬታዎች እየተሰሙ ነው ዋዜማ ራዲዮ-ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያላቸው ግንኙነት ውስብስብና ስላም የራቀው ብሎም በሁለት ታላላቅ ጦርነቶች የታጀበ ነበር። ያለፉት አመታት ሶማሊያ በደረሰባት ውስጣዊ ቀውስ ለኢትዮጵያ አደጋ የምትጋብዝ…

ለክፉ ጊዜ የሚኾኑ አዲስ የፖሊስ ሠራዊት አባላት ምልመላ ተጀመረ

ዋዜማ ራዲዮ- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እድሜያቸው ከ18 እስከ 25 የሚኾኑ ሥራ አጥ ወጣቶችን በተጠባባቂ ፖሊስ አባልነት ለመመልመል ያወጣው ማስታወቂያ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችን ትኩረት ስቧል፡፡ በወረዳና ክፍለ ከተማ ማዕከሎች፣…

መንግሥት ከአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮች ጋር እየተወያየ ነው

አመጽ ቀስቃሽ የታክሲ ጥቅሶችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ተነግሯቸዋል ዋዜማ ራዲዮ- ካለፈው ሳምንት ሚያዚያ 11 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ስቴዲየም በሚገኘው የመንገዶች ባለሥልጣን አዳራሽ በፈረቃ ከመንግሥት ሰዎች ጋር እየተወያዩ የሚገኙት ባለ ኮድ አንድ…

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2017 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና ሆኖ ተመረጠ

ዋዜማ ራዲዮ- ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም አለም አቀፍ ፕሬስ ኢንስቲትዩት ከቪየና በወጣው መግለጫ መሰረት እስክንድር ነጋ የግል ህይወታቸውን መስዋዕት በማድረግ ለንግግር ነፃነት የጎላ አሰተዋፅዎ ያበረከቱ ጋዜጠኞችን ለማክበር እና…

ግብፅ የኢትዮጵያን እጅ ጥምዘዛው እየሰመረላት ነው

ዋዜማ ራዲዮ- በዓባይ ወንዝ ሳቢያ አንዴ ሲከር ሌላ ጊዜ ሲለዝብ የነበረው የኢትዮጵያና የግብፅ ውዝግብ አሁን አዲስ መልክ ይዟል። በተለይ ያለፉትን ስድስት ወራት ግብፅ ያለ የሌለ አማራጮቿን ተጠቅማ ኢትዮጵያን ለማስገደድ ጥረት…

ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የ87 ባለኮከብ ሆቴል ገንቢዎችን ፍቃድ ሊሠርዝ ነው

ዋዜማ ራዲዮ-የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ባለኮከብ ሆቴል ለመገንባት የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ 87 ከፍተኛ ባለሐብቶችን ፍቃድ ለመሰረዝ በዝግጅት ላይ ነው፡፡  በተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/2004 መሠረት የባለኮከብ ሆቴል…

ኢቴቪን የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች መበራከት በእጅጉ አሳስቦታል ፣ለለውጥ የሚረዳ ጥናት ጀምሯል

ዋዜማ ራዲዮ- ከሁለት ዓመት በፊት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዮ የልደት በዓሉን በድምቀት ያከበረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቢሲ) ሁለት ወቅታዊ ፈተናዎች ከፊቱ እንደተደቀኑበት አመነ፡፡ እነዚህም የጣቢያው የማስታወቂያ ገቢ ድርሻ ከጊዜ ወደ…

ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አወዛጋቢውን ድንበር ለማካለል ተስማሙ

ዋዜማ ራዲዮ-የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል መንግስታት ለወራት የግጭት ሰበብ ሆኖ የቆየውን ድንበር ለማካለል ስምምነት ተፈራረሙ። የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶች- የኦሮሚያ ክልል ፕ/ት ለማ መገርሳና የሱማሌ ክልል ፕ/ቱ አብዲ መሀመድ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትሩ…

አዲስ አበባ እስከ ሰኔ መጨረሻ ነባር ሰፈሮቿን በጥድፊያ ታፈርሳለች

ከንቲባ ድሪባ በጥቂት ቀናት 1ሺህ 300 ቤቶችን ያፈረሰውን ቂርቆስ ክ/ከተማን አወደሱ ዋዜማ ራዲዮ-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ተጨማሪ ወራት መራዘሙን ተከትሎ የአዲስ አበባ ካቢኔ አስቀድሞ የያዘውን ቤቶችን በስፋት የማፍረስ ምስጢራዊ እቅድ…