Tesfalem BW

ዋዜማ ሬድዮ/UPDATED/– የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ጋዜጠኞቹ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ እና አስማማው ሃይለጊዮርጊስ ከእስር ተፈቱ።ኤዶምና ማህሌት በይፋ ከቃሊቲ እስር ቤት የሚወጡት ነገ ማለዳ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ዛሬ ማምሻውን “ክሳችሁ ተቋርጧል፣ አሁኑኑ እቃችሁን ይዛችሁ ውጡ” የተባሉት ታሳሪዎች፣ የመውጫ ደረሰኝ ተቋርጦላቸው ከቂሊንጦ እስር ቤት ወጥተዋል። ከእስር ስለመፈታታቸው አንዳችም ፍንጭ አስቀድሞ እንዳልተሰጣቸው ታውቋል። “በታሰርንበት ሁኔታ ተፈታን” ብሏል አንዱ ተፈቺ።የቀሪዎቹ 4 ጦማርያን ክስ የሚቀጥል መሆኑን ፍትሕ ሚኒንስቴር አስታውቋል።

ዘጠኙ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ከታሰሩ ዛሬ 440ኛ ቀናቸው ነው። መንግሥት በሽብር ወንጀል ከስሻቸዋለሁ ሲል መቆየቱ ይታወቃል፣ መታሰራቸውም ሆነ የፍርድ ሒደቱ በመንግሥት ላይ በአገር ቤትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትችት ሲያስከትልበት ቆይቷል። ቸር ወሬ ነው።