ዋዜማ ራዲዮ- በኢትዮጵያ እየተፈፀመ ላለው ብሄርን ያማከለ ግጭት ከወቅታዊ ጉዳዮች በዘለለ ተቋማዊና ህገመንግስታዊ መደላድል እንዲያገገኝ ያደረጉ ምክንያቶች አሉ። አሁን በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል መንግስታት መካከል የተለኮሰው ግጭት ያለፉትን ሶስት አመታት አንካሳ ሆኖ ለሰነበተው ህወሀትና የማዕከላዊ መንግስቱ ትርፍ እንዲያስገኝ ተደርጎ የተዘጋጀ ተውኔት ነው። ተውኔቱ ከታለመለት ግብ አልፎ ከሄደ ሀገሪቱ ትልቅ ፈተና ይጠብቃታል። ዋዜማ ራዲዮ በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን አሰናድታለች። ከታች አድምጡት
በፌደራሉ የደህንነትና ወታደራዊ ይሁንታ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ያለው ይህ ግጭት ስንቆታል ያለውን ፖለቲካዊ ተልዕኮ አርጋው አሽኔ ይመለከተዋል። ቻላቸው ታደሰ ደግሞ በሀገሪቱ በተፈለገ ጊዜ ግጭት ለመቀስቀስ ቀዳዳ የሆኑ መዋቅራዊና ህገመንግስታዊ አደርጃጀቶች አሉ ይለናል። በቅድሚያ አርጋው፣ ከግጭቱ ማን ምን ያተርፋል?