ዋዜማ ራዲዮ- በአዲስ አድማስ ጋዜጣ አምደኛነት ለረዥም ዓመታት የዘለቀው ኤፍሬም እንዳለ ነው ይህን የሬይሞንድ ጆንስን መጽሐፍ ‹‹የአድዋ ጦርነት›› በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተረጎመው፡፡ ኤፍሬም ይህን የመጽሐፍ ትርጉም ሥራ የጀመረው ከበርካታ ዓመታት በፊት እንደነበረና የዚህ መጽሐፍ ሌላ ትርጉም በጊዜው በድንገት ገበያ ላይ በመዋሉ የርሱን ትርጉም ኅትመት እንዲዘገየ እንዳደረገ መግቢያው ላይ ገልጧል፡፡
በአተረጓጎም ስልቱ ነጻ የአተረጓጎም ዘዬን እንደመረጠና ለአገራችን አንባቢ በሚስማማ መልኩ እንዳዘጋጀው የገለጠው ተርጓሚው በተለይም የእንግሊዝኛ መጽሐፉ ደራሲ ሬይሞንድ ጆናስ ዋቢ መጽሐፍ መዘርዝር የያዙ 61 ገጾችን እንደቀነሰ ገልጧል፡፡
በአድዋ ድል 121ኛ ዓመት ዋዜማ ለገበያ የቀረበው ይህ የትርጉም ሥራ 21 ምዕራፎች ሲኖሩት 287 ገጾችን ይዟል፡፡ መጽሐፉ በፋርኢስት ማተሚያ ቤት የተራባ ሲኾን በ80 ብር ዋጋ ክብሩ መጽሐፍት መደብር ያከፋፍለዋል፡፡
40 የሚኾኑ ምስሎች የተካተቱበት ይህ መጽሐፍ በአጼ ቴዎድሮስ ላይ ከተካሄደው ዘመቻ አምፒር ጀምሮ ከአድዋ ጦርነት ማግስት ስለነበረው የሚኒሊክ ይቅር ባይነት ይተርካል፡፡
432 ገጾች ያሉት የእንግሊዝኛ ቅጂውን ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ መጀመርያ በ2011 እ.አ.አ ከዚያም በ2005 በድጋሚ አሳትሞታል፡፡