ዋዜማ ራዲዮ-በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የተቃውሞ ስልፍ ሳይካሄድ ቀርቷል። ለሰልፉ አለመካሄድ ዋና ምክንያት የመንግስት ማስፈራሪያና ተቃዋሚዎች ላይ ማናቸውም እርምጃ ለመውሰድ መዛቱ ነበር። የአዲስ አበባው ስልፍ አለመሳካት በሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ያዳክመው ይሆን አርጋው አሽኔ ዘገባ አለው-እዚህ ያድምጡት
የተቃውሞ ሰልፉ አለመሳካት ለገዥው ፓርቲ የልብ ልብ የሚሰጥና የእስካሁኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ሲሉ ለዋዜማ አስተያየታቸውን የሰጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ተናግረዋል።
ምንም እንኳን የሰልፉ መቅረት ለገዥው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ጥሩ አጋጣሚ ቢመስልም በሀገሪቱ ያለውን ተቃውሞ በመሰረታዊነት ሊቀይረው የሚችል አይደለም። ከህዝባዊ አመፁ ባሻገር ገዥው ፓርቲ ሊጠገን የማይችል ውስጣዊ የመሰንጠቅ አደጋ አንዣቦበታል።
ከሳምንት በፊት በማህበራዊ ድረ ገፃች ቀጠሮ የተጠራበት የአ.አን የተቃውሞ ሰልፍ በባለቤትነት የጠራ የፓለቲካ ፓርቲ ያለመኖሩ በመንግስት ከተነገረው ማስፈራሪያና ዛቻ በተጨማሪ የተቃውሞ ሰልፉ ለመቅረቱ ምክንያት መሆኑንም ፓለቲከኞቹ ገልፀዋል።