የሶማሊያ ታጣቂዎችን በመርዳት ተከሳ በመንግስታቱ ድርጅት ማዕቀብ ስር የምትገኘው ኤርትራ በቅርቡ ደግሞ በሀገሪቱ ለሀያ አምስት አመታት ተፈፅሟል ለተባለው የመብት ጥሰትና ግፍ መሪዎቿ በዓለም ዓቀፍ መድረክ ለፍርድ እንዲቀርቡ ገለልተኛ አጣሪ ኮምሽኑ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል። በሽኘነው ሳምንት የገለልተኛ አጣሪ ኮምሽኑ ሪፖርት ወደ ስብዓዊ መብት ካውንስሉ ተመርቷል። ሪፖርቱን በካውንስሉ እንዲፀድቅ ለውይይት ያቀረቡት ሶማሊያና ጅቡቲ ናቸው። ኤርትራ ከዜጎቿና ከደጋፊ ወዳጆቿ የተሰባሰበ ሁለት መቶ ሺህ የተቃውሞ ፊርማ ለካውንስሉ አስገብታለች። ቀጥሎስ ምን ይጠበቃል? የተፈራው ዱብ ዕዳ በኤርትራ መሪዎች ላይ ሊወርድ ይሆን? ኤርትራ በከፍተኛ የዲፕሎማሲ መከላከል ስራ ተጠምዳ ስንብታለች።ተከታዩ የአርጋው አሽኔ ዘገባ ተጨማሪ ዘገባ አለው። ያድምጡት