(ዋዜማ)- እንደ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ግምገማ ኢትዮዽያ ከመቼውም በላይ የፀጥታና ደህንነት አደጋ አንዣቦባታል፣ ይህን አደጋ በድል ከተሻገርነው ኢትዮዽያ በማያዳግም መልኩ ጠንካራ ሀገር ሆና ትወጣለች። የሳዑዲ አረቢያ የውሀቢ እስልምና ዘውግ የደቀነው አደጋ ከወዲሁ ሊታሰብበት የሚገባ ነው ባይ ናቸው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የጥናት ፅሁፍም አላቸው። አደጋዎቹን መገንዘብና መፍትሄዎቹ ላይ በርትቶ መረባረብ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያሰምሩበታል። ከኤርትራ ጋር ያለንን ግንኙነት በማሻሻል ለአደጋ ተጋላጭነታችንን መቀነስ ይቻላል ይላሉ የጥንቱ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ምሩቅና የጦር መኮንን የሆኑት ሻለቃ ዳዊት። በኢትዮዽያ በጦርነትና በሀይል የሚመጣ ለውጥ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ሊያመጣ ይሳነዋል ።ሻለቃ ዳዊት አሁንስ ምን እየሰሩ ነው? ሁሉንም ከራሳቸው አፍ ስሙት፣ ዋዜማን አድምጡ አጋሩ