(ዋዜማ ራዲዮ) በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ መድረሻው የት ይሆን? ብሎ የማይጠይቅ የለም። በእርግጥስ አመፁ የስርዓት ለውጥ ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ አንዳንድ ሀሳቦችን ታሳቢ ማድረግ ጠቃሚ ሳይሆን አልቀረም። አመፁ መሪ ይፈልጋል ። በኢህአዴግ አፈና ውስጥ መሬት ሆኖ ይህን ተቃውሞ የሚመራ የሚኖርባት ፈተና ከባድ ነው። መሪ አልባ አመፅስ ያዋጣል? ተቃውሞው “ያልተደራጀና ግብታዊ” መሆኑ ጠቃሚ ነበር የሚሉ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ሌሎች ደግሞ “ተቃውሞው በወጉ ቢደራጅ” ኢህአዴግ ሊቋቋመው የማይችል ማዕበል መፍጠሩ አይቀሬ ነው ይላሉ። በዚህ በሁለት ክፍል ውይይት የተወሰኑ ጉዳዮችን እናነሳለን። ተወያዩቻችን የሚያነሱትን ሀሳብ አድምጡና የናንተንም አጋሩን።
ቀዳሚ የነበረውን ክፍል አንድ ላላደመጣችሁ እነሆ ማስፈንጠሪያው LINK http://wazemaradio.com/?p=1567