በሶማሊያ አልሸባብ ሁለት የመሰንጠቅ አደጋ አንጃቦበታል። የክፍፍሉ መንስዔ አይ. ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድንን ተቆራኝተን አብረነው መስራት አለብን በሚሉና የለም ከእናት ድርጅታችን አልቃይዳ መለየት የለብንም በሚሉት መካከል ነው።
አልቃይዳ በአለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብና የሰው ሀይል የድጋፍ ምንጩ በመዳከሙ እንደ አልሸባብ ላሉ አጋር ድርጅቶቹ በቂ ድጋፍ ማድረግ አልተቻለውም። ይህን የተመለከተው አይ. ኤስ የተሻለ የገንዘብ ድጋፍና ማባበያ በመስጠት እግሩን በምስራቅ አፍሪቃ ለመትከል አቆብቁቦ ይገኛል።
በጉዳዩ በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ የተወስኑ የአልሸባብ ውታደሮችና አንድ ከፍተኛ አመራር ክድርጅታቸው ከድተው በኪስማዮ መሽገዋል። የአይ ኤስ ውደ ቀጠናው መግባት ለኢትዮዽያ ፈተናም ዕድልም ይዞ ሊመጣ ይችላል። አርጋው አሽኔ ያዘጋጀውን ዘገባ አድምጡት።