ታሪክ ከትላንት ይልቅ ለዛሬ ፋይዳው እጅጉን የጎላ ነው። ታሪክን በቅጡ አለመረዳትም ይሁን አዛብቶ ማቅረብ የውዝግብ ብሎም የግጭት መንስኤ ሲሆን ይስተዋላል። የኢትዮዽያ ታሪክም ከዚህ የተለየ አይደለም። ታሪክ እንዴት ይፃፋል ? በማን ይፃፋል? የማንስ ታሪክ ነው የተረኩ እምብርት መሆን ያለበት? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት በተወሰነ ደረጃ ስለጉዳዩ ውስብስብነት ፍንጭ ይሰጣል። የዋዜማ እንግዶች ጉዳዩን ጠለቅ ብለው ተመልክተውታል። አድምጡት…አጋሩት