HMD Demeke Mekonen( ዋዜማ ራዲዮ) እንደ መንግስት መረጃ ቢሆን ኖሮ! ኢትዮዽያ በ5 አመት ውስጥ ያስመዘገበችውን ያህል የግብርና ምርት ዕድገት ለማስበዝገብ ህንድ በአረንጓዴ አብዮት ዘመን (1975-1990) አስራ አምስት አመት ፈጅቶባታል። አለምን ባስደመመው የቻይና ኢኮኖሚ ሽግግር (ትራንስፎርሜሽን) ወቅት ቻይና ኢትዮጵያ በአምስት አመት ውስጥ ያስመዘገበችውን ያህል የግብርና ዕድገት ላይ ለመድረስ አስር ዓመታት (1960-1970) ፈጅታለች።

 

እንደ መንግስት መረጃ ቢሆን ኖሮ! የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብል ተረፈ ምርት ብቻውን ኬንያና ዩጋንዳን ለዓመት በላይ መቀለብ ይችላል። ታዲያ ለምን ይርበናል? ለምን ልመና አደባባይ እንቆማለን? በዚህ የውሸት ፍርግርግ የከረቸመን ኢህአዴግ መጠየቅ የለበትም? የዋዜማ እንግዶች የኢትዮዽያ የሰብል ምርት ዕድገት የተጋነነ፣ አጠራጣሪና ሀሰተኛ ነው ይላሉ ። አድምጧቸው