ዋዜማ ራዲዮ- ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በዳላስ ቴክሳስ በሚደረገው የኢትዮጵያው ያን የስፖርት በዓል ላይ የሚጋበዙ ከሆነ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ እንግዳ በመጋበዝ ሊከስት የሚችለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባ አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ግብረ ሀይል አሳሰበ።
ግብረ ሀይሉ ለዋዜማ ባደረሰው መግለጫው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን መጋበዝም ሆነ አለመጋበዝ የሚያስከትለውን ልዩነት ለማስወገድ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ ዶ/ር መራራ ጉዲና አልያም አቶ አንዷለም አራጌ ቢጋበዙ የሰፖርት ፌደሬሽኑ ከወገንተኝነት ነፃ ያደርገዋል።
አሁን እየተካሄዱ ያሉ ዘመቻዎች በዚህ ከቀጠሉና ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ብቻ የሚጋበዙ ከሆነ የዲስፖራው ማህበረሰብ በእጅጉ እንደሚከፋፈል፣ የስፖርት ፌደሬሽኑም የከፋ የክፍፍል አደጋ እንደሚገጥመው ግብረ ሀይሉ አስጠንቅቋል።
በበዓሉ ላይ ተቃውሞ የሚኖር ከሆነ ዝግጅቱን በወጉ ለማካሄድ ተፀጥታ ስጋት የሚኖር ሲሆን የተሳታፊ ኢትዮጵያውያንን ቁጥርም እንደሚቀንሰው ያለውን ስፋት ግብረ ሀይሉ በመግለጫው አስፍሯል።
ግብረ ሀይሉ አስተያየቱን ለፌደሬሽኑ መላኩንም ገልጿል።
የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ የስልሳ አንድ የቦርድ አባላቱን ድምፅ እያሰባሰበ ነው።