ዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮዽያ መንግስት አዲስ ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።
የሁለቱ ሀገሮች የጋር ስብስባ በተደረገበት የአዲስ አበባው የሚንስትሮች የጋራ ስብሰባ ላይ የሁለቱ ሀገሮች ወታደራዊ ሹማምንት አዲስ የትብብር ስነድ መፈረማቸውን ከአፍሪኮም የተላከልን መረጃ ያመለክታል። ስምምነቱ ወታደራዊ ድጋፍን (የጦር ማሳሪያ ድጋፍ፣የመረጃ ልውውጥና ስልጠናን ይመለከታል)። በተለይ የሶማሊያ የፀረ ሽብር ትብብር ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ተደርሷል። በዚህ ስብሰባ ላይ ኢትዮዽያን በመወከል የኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ሳሞራ የኑስና የመከላከያ ሚንስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ የተካፈሉ ሲሆን አሜሪካንን የወከሉት ምክትል መከላከያ ሚንስትር አማንዳ ዶሪና የአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ ጀነራል ዴቪድ ራድሪጉያዝ አዛዥ ናቸው።
የሁለቱ ሀገሮች የሚንስትሮች የጋር ስብሰባ በዴሞክራሲና ስብአዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ ሌላ ዝግ ስብሰባ አድርጓል።