ዋዜማ- በደቡብ ክልል በሰላም ሰባኪነትና በአስታራቂነት ከአካባቢያቸው አልፈው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላም አምባሳደር የሆኑት የጋሞ አባቶች ልክ የዛሬ አመት ለበጎ ተግባራቸው አስር ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸው ነበር።


ሽልማቱን ያበረከተው አንቴክስ ኢትዮጵያ ቴክስታይል የተባለ ኩባንያ ሲሆን ገንዘቡን ማስረከቡንም ለዋዜማ አረጋግጧል።
የጋሞ አባቶች እንደሚሉት ገንዘቡት የተቀበለው የጋሞ ዞን አስተዳደር ነበረ። ሽልማቱን አዲስ አበባ ላይ ተቀብለው ወደ አርባ ምንጭ ከተመለሱ በኋላ ግን ገንዘቡ የት እንደደረሰ ማወቅ እንዳልቻሉ የሀገር ሽማግሌዎቹ ተወካይና የጋሞ ማህበረሰብ ንጉስ ካዎ ታደሰ ዘውዴ ነግረውናል።

እስካሁን በጉዳዩ ላይ ዝምታ የመረጡት የሰላም ሰባኪ ሆነው ሳለ በገንዘብ ጉዳይ ተወዛግበው አደባባይ መቆም አሳፋሪ ነው ብለው ሰለሰጉና ጉዳዩ ከዛሬ ነገ ይፈታል ብለው ስላመኑ መሆኑን ነግረውናል። አሁን ግን ጉዳዩን ሕዝብ ሊያወቀ ይገባል በሚል ለመናገር መወሰናቸውን አስረድተዋል።
የጋሞ ዞን አስተዳደር በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጠን ላቀረብንለት ጥያቄ ራሳቸው አባቶቹ ይጠይቁኝ የሚል መልስ በመስጠት ስልክ ዘግተውብናል። ዝርዝሩን ከራሳቸው አንደበት ተመልከቱት/አድምጡት