የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባልሥልጣን ዛሬ ቅዳሜ ጥር 16፣ 2018 ዋዜማ ሚዲያን/ሬዲዮን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ ተመልክተናል። 

ባለሥልጣኑ ሐሙስ ዕለት ፈቃዳችንን እንድንመልስ ባዘዘን መሠረት ዛሬ ይህንኑ አድርገናል። መግለጫው የተሰጠው ይህንን ባደረግን በሰዓታት ውስጥ ነው።

እርምጃው በማንኛውም መመዘኛ ትክክል ነው ብለን አናምንም። አሳዝኖናልም። ዝርዝሩን በሚገባ አጢነን አስፈላጊና ጠቃሚ ከሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንሰጣለን፤ ሌሎች ሕጋዊ አማራጮችን እንከተላለን። 

ባለሥልጣኑ ባወጣው መግለጫ፣ ዋዜማ ሚዲያን “የአገርን ጥቅም” አደጋ ላይ በመጣል እና የጋዜጠኝነት ሥነምግባርን ባለማክበር ወንጅሏል። እነዚህን ክሶች የኢትዮጵያን ሚዲያ ለሚከታተሉ ተደራሲዎች፣ ታዛቢዎች እና ባለሞያዎች የሕሊና ፍርድ እንተዋለን። 

የዋዜማ ሚዲያ አመራር

 ጥር 16፣ 2018