(ዋዜማ ራዲዮ) ህዝባዊ አመፁ በገዢው ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎች ዘንድ አዳዲስ ዕድሎችና ፈተናዎችን ይዞ መጥቷል።
የኦሮሞ ብሄረተኛ ፓርቲዎችም ሆኑ የአንድነት ሀይሎች ወደተባበረ የትግል ስልት የሚያስኬድ መግባባት የላቸውም። ይህም ህዝባዊ አመፁ በቀላሉ የአፋኙ መንግስት ሰለባ እንዲሆን አድርጎታል። የፖለቲካ ቡድኖቹ ወደ ማግባባት ለመምጣት የሚያደጉት ሙከራ የሚያስከፍለው ዋጋ ይኖራል።
ገዢው ፓርቲ በኦህዴድ እየተነሳ ያለውን ቅሬታ ለማዳፈንና አፈንጋጮችን ለማስወገድ የውስጠ-ፓርቲ ዘመቻ መጀመሩም አይቀሬ ነው።
አርጋው አሽኔ ዝርዝር ዘገባ አለው አድምጡት