Major Dawit W Giorgis one of the facilitator
Major Dawit W Giorgis one of the facilitators
  • “አንድ አማራ” የሚል ድርጅትም አቋቁመዋል

ዋዜማ ራዲዮ- ከዚህ ቀደምበተበታተነ መልኩ የሚካሄደውን ትግል በማቀናጀት በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመቀየርም ያለመ “አንድ አማራ” በሚል በአዲስ አደረጃጀት መጥተዋል።

የአማራ ዘውጌ ፖለቲከኞችን ወደ አንድ መድረክ እንዲመጡ ለማድረግ ላለፈው አንድ አመት ገደማ ድርድር እና ዝግጅት ሲደረግ እንደነበር መስራቾቹ ይናገራሉ።

የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን ህልውና የማጥፋት ዘመቻ ለመመከት የሚሰራ እንድሆነ የተነገረለት ይኸው አዲሱ የአማራ የብሔር ድርጅት “አንድ አማራ” በሚል ስያሜ ራሱን አደራጅቶ  የተጠናከረ ትግል ለማደረግ እና በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመቀየር ራዕይ እንዳለው ለመገናኛ ብዙኃን የላከው መግለጫ ይናገራል።

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስና ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ይህን ጥምረት ለማሳካት በአደራዳሪነት መሳተፋቸውን የዋዜማ ሪፖርተር ይገልፃል።

የአማራ ህዝብ ከብሔር አሰላለፍ ይልቅ ህብረ ብሔራዊ ትግል ይዞ መቆየቱን የሚናገረው የአንድ አማራ መግልጫ የአማራው ነገድ ራሱን ለመከላከል፣ ህልውናውን ለማቆየት በብሔር ማንነቱ ዙሪያ ተሰልፎ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኗል ይላል።

አንድ አማራ የሚልውን ድርጅት ለመመሰረት አስራ አንድ ወራት የፈጀ የባለድርሻዎች ውይይት ሲደረግ እንደነበረ መግለጫው ያሰረዳል፡፡ ሆኖም በውይይቱ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ሁሉንም የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና የሲቪል ሃይሎችን ግንባር በአንድነት ለማሰባሰብ ባይቻልም የትግሉን አሰፈላጊነት በተረዱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አማካኝንት “አንድ አማራ” እደተመሰረተ ይናገራል።

“አንድ አማራ” ከየትኞቹ የአማራ የፖለቲካ ሃይሎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች እንደተመሰረተ መግለጫው ባያትትም ወደፊት ሰለድርጅቱም ሆነ ድርጅቱ ሰለቆመለተ አላማ ዝርዝር መረጃዎችን እንድሚሰጡ እና በቅርቡም ድርጅታዊ ጉባዔ እንድሚያደርጉ መግለጫው ይናገራል።

አማራው ነገድ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመከላከል በጋራም ይሁን በግል ከኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ለሆኑ በራችን ክፍት ነው ይላሉ የአንድ አማራ መስራቾች። [ተጨማሪ የድምፅ ዝርዝር ዘገባ ከታች ያድምጡ]

https://youtu.be/XX7J8p9wspI