Jemal Dirye, One of the founders of the Movment
Jemal Dirye, One of the founders of the Movment

ዋዜማ ራዲዮ- በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ህዝብ ለፍትህና ለዕኩልነት የሚያደርገውን ትግል ለማገዝና ለማስተባበር አዲስ የሶማሌ ህዝብ ንቅናቄ መመስረቱን አስተባባሪዎቹ ይፋ አድርገዋል።
“የሶማሌ ክልል ፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ” ተብሎ የሚጠራው ይህ ድርጅት የሶማሌ ህዝብን ትግል ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ጋር ለማስተሳሰር አላማ ያለው መሆኑም ተገልጿል።
በስውዲን ስቶኮሆልም ዛሬ ይፋ የተደረገው ህዝባዊ ንቅናቄ በአፋጣኝ ወደሰራ ገብቶ በክልሉ እየተፈፀሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚያጋልጥና ህዝቡን የማንቃትና የመደራጀት ስራ እንደሚያከናውንም አመልክቷል።
በክልሉ ለአራት አስርት አመታት እየተንቀሳቀሰ ካለው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር በሚያስማሙት ጉዳዮች ላይ ተግባብቶ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውና በዋነኝነት ግን የሶማሌ ህዝብን ፍላጎትና ምኞት ለቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በማሳወቅ ላይ አተኩሮ ለመስራት መዘጋጀቱን አስተባባሪዎቹ ለዋዜማ ተናግረዋል።

srm-logo
“ለዘመናት የዘለቀ መገለልና በጥርጣሬ መተያየት ስፍኖ ቆይቷል፣ አሁን ጊዜው የሶማሌ ህዝብ በማንነቱ ተገቢው እውቅና ተሰጥቶት በመረጠው መንገድ የሚኖርበት ነው”  ሲሉ ከኣአስተባባሪዎቹ አንዱ ጀማል ድሪዬ ካሊፍ ለዋዜማ ገልፀዋል።
ጀማል ድሪዬ  የምክር ቤት አባል የነበሩ ሲሆን ስርዓቱን ትተው  በአውሮፓ በስደት ይኖራሉ።